የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተጀመረው የገበያ ማረጋጋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

May 6, 2025

IDOPRESS

ደብረ ማርቆስ ፤ሚያዚያ 27/2017 (ኢዜአ) ፡-አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተጀመረው የገበያ ማረጋጋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በደብረ ማርቆስ ከተማ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ተጓዥ የንግድ ትርዒትና ባዛር ዛሬ ተከፍቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ በወቅቱ እንደገለጹት የንግድ ትርዒትና ባዛር መዘጋጀቱ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ ግብይት ለማካሄድ የሚያስችል ነው።

ይህም ህገወጥ ደላሎች በግብይቱ ላይ የሚፈጥሩትን ችግር በመቅረፍ ሸማቹ ማህበረሰብ የሚፈልገውን ምርት በአንድ ቦታና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

"መሰል የንግድ ትርዒትና ባዛር ዝግጅቶች አምራችና ሸማቹን በማገናኘት የገበያ መረጋጋትን ስለሚፈጥሩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል" ብለዋል።

በባዛሩ የሚሳተፉ አምራች ድርጅቶች፣ ኢንተርፕራይዞችና አቅራቢዎችም የገበያ ትስስር በመፍጠር ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ መለሰ የንግድ ትርዒትና ባዛሩ የአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማህበር የደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ ከአጋር ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

የንግድ ትርኢትና ባዛሩ የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት በማለም መዘጋጀቱን ጠቅሰው ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚቆይና በክልሉና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ከ80 በላይ የንግድ ድርጅቶች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025