የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የእምድብር ከተማ ሁለንተናዊ እድገት እየተፋጠነና ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

May 7, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፤ ሚያዝያ 28/ 2017 (ኢዜአ)፡-የከተሞችን እድገት ለማፋጠን በተሰጠው ትኩረት የእምድብር ከተማ ሁለንተናዊ እድገት እየተፋጠነና ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

በከተማዋ በህዝብ ተሳትፎ የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄ የሚመልሱና ገጽታዋን የሚቀይሩ የመሰረተ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል።

የልማት ሥራዎቹን አስመልክቶ ለኢዜአ አስተያየታቸውን ከሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ሰውዳ ሁሴን ቀደም ሲል የከተማዋ እድገት አዝጋሚ እንደነበር አስታውሰዋል።


ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከተማዋን ለማልማት ትኩረት በመሰጠቱ ሰፋፊ መሰረተ ልማቶች መከናወናቸውንና በዚህም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የከተማዋን አድገት ለማፋጠን ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች መካከል የመንገድ ሥራዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፣ በቀጣይም የነዋሪውን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል።


ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ትዕዛዙ ናማጋ በበኩላቸው እንዳሉት በከተማዋ ሆቴሎች፣ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ መንገድና ትላልቅ መሸጋገሪያ ድልድዮች ማስተር ፕላንን ጠብቀው እንዲገነቡ መደረጉ ከተማዋ ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን አድርጓታል።

አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በአንድ አካባቢ በመገንባት እና በማዘመን ተገልጋዩን ከብልሹ አሰራርና እንግልት መታደግ በመቻሉ ተጠቃሚ ነን ያሉት ነዋሪው፣ የከተማዋን ልማት ለማፋጠን በሚሰሩ ሥራዎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።


የእምድብር ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተክሌ ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ተመራጭ ለማድረግ ነዋሪዎችን በማስተባበር መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

ብልሹ አሰራርን በማስቀረት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በተሰጠው ትኩረትም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የአንድ ማዕከል የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መስጫ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።


የእምድብር ከተማ ከንቲባ አቶ ግምባሩ በርጋ በበኩላቸው፣ በከተማው የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በተሰሩ ሥራዎች ችግሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየተፈታ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ለዚህም በከተማ አስተዳደሩ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድ፣ የፍሳሽ ማውረጃ ቱቦ፣ የድልድይ፣ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት መስጫ ግንባታዎችን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ከመሰረተ ልማቶች ባለፈ ለንግድ እና ለኢንቨስትመት ቦታዎችን በማመቻቸት በተቀናጀ የግብርና እንቅስቃሴ በርካታ ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።


የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ለእምድብር ከተማ አዲስ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ባለፉት አምስት ዓመታት አበረታች የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።

የማዘጋጃ ቤትና የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን ባለፈ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

መንገድና ሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እያስቻሉ መሆኑንም አቶ ላጫ ተናግረዋል።

የእምድብር ከተማ በጉራጌ ዞን ካሉት ከተሞች በፈርጅ ሦስት የከተማ አስተዳደርነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025