የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ለግብርናው ዘርፍ አቅም የሚፈጥሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ለግብርናው ዘርፍ አቅም የሚፈጥሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶስት ዓመት በፊት ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡበት ይገኛል፡፡

በንቅናቄው ገቢ ምርትን ከመተካት አንጻር በ2014 በጀት አመት የተመዘገበውን 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በ2017 ዘጠኝ ወራት ወደ 4 ነጥብ 67 ቢሊየን ዶላር ከፍ ማድረግ ተችሏል፡፡

በዚህም ተኪ ምርት በማምረት ኢትዮጵያ ምርት ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፡፡

ለዚህ ስኬት ተኪ ምርትን የሚያመርቱ የፈጠራ ባለሙያዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው።

ኢዜአ በአራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ ተገኝቶ ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው የቀረቡ አምራቾችን ተዘዋውሮ አነጋግሯል።

ከነዚህ መካከል ከአራት የስራ ባልደረቦቹ ጋር በመተባበር የተፈጥሮ ማዳበሪያ የሚያመርት ማሽን የሰራው በአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማንዩፋክቸሪንግ ዘርፍ አሰልጣኙ ተሾመ ለማ ይገኝበታል፡፡

አሰልጣኝ ተሾመ ለማ አርሶ አደሮች የግብርና ስራቸውን ውጤታማ ለማድረግና ለማዘመን በሚያደርጉት ጥረት የዘወትር ፈተናቸው የማዳበሪያ እጥረት መሆኑን መገንዘባቸው ፈጠራውን ለመስራት እንዳነሳሳቸው ነው የተናገረው።

የሰሩት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረቻ ማሽን በኤሌክትሪክ ወይም በእጅ በማንቀሳቀስ ማዳበሪያውን ማምረት እንደሚቻል ነው የተናገሩት።

ማሽኑ ልዪ ልዩ ተረፈ ምርቶችን በመፍጨት በአንድ ቀን 12 ኩንታል የሚገመት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረት እንደሚችል ጠቅሰዋል።

በሀዋሳ ከተማ በኦሶ ማሽነሪ ኢንተርፕራይዝ የፕሮዳክሽን ማናጀር የሆነውና የመካኒካል ኢንጅነር ምሩቁ ኤርሚያስ ሀይሉ በበኩሉ ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቡናን ቆልቶ በመፍጨት የሚያሽግ ማሽን ከሶስት ባልደረቦቹ ጋር መስራቱን ይናገራል።

ቡናን በጥሬው ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ እሴት በመጨመር የመላክ አቅማችንን ለምን ማጎልበት አንችልም በሚል ቁጭት የፈጠራ ውጤቱን ማበልጸጋቸውን ለኢዜአ አስታውቋል።

የቡና ፕሮሰሲንግ ማሽኑ ቡና ከመቁላት ጀምሮ ተፈጭቶ እስከ ማሸግ ያለውን ሂደት የሚያጠቃልል መሆኑን አስረድቷል፡፡

የፈጠራ ውጤታቸው መሰል ማሽኖችን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት ረገድ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው ብሏል።

አሰልጣኝ ተሾመ ለማ እንደ ሀገር ያለንን የፈጠራ ተሰጥኦ በትምህርት በመደገፍ ሀገራችን ከውጭ የምታስገባቸውን ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ የማንተካበት ምንም ምክንያት የለም ብሏል።

ኢንጅነር ኤርሚያስ ሀይሉ በተሻለ እና በዘመነ መንገድ ቡናን ከሰው ንኪኪ በጸዳ መልኩ ማዘጋጀት የሚያስችለውን ማሽን በስፋት ለገበያ ለማቅረብ በትኩረት የምንሰራበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025