አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደጉን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ሶስተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ መክፈታቸው ይታወሳል።
የኤክስፖው አካል የሆነ የፓናል ውይይት "በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊና ቅንጅታዊ አሰራር የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ማሳደግ" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሒዷል፡፡
በፓናል ውይይቱ የፋይናንስ፣ የጉምሩክ፣ የቴክኖሎጂና ቢዝነስ ድጋፍ፣ ለአምራች ዘርፉ አስተማማኝ የሎጂስቲክስ አገልግሎት መዘርጋት፣ የግብዓትና ሸቀጦች ፍሰትን ማሳለጥ የሚሉ ጉዳዮች ተዳሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግስት አምራች ኢንዱስትሪውን ለማበረታታት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡
በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ህገ-ወጥ ንግድን ያስቀረና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሎጂስቲክ አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ የተወሰዱ እርምጃዎች የዘርፉን ውጤታማነት ማሳደጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በፊት ይፈጸም የነበረው ህገ-ወጥ የእንስሳት ንግድ በምርታማነታቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥር እንደነበርም አንስተዋል፡፡
ችግሩን ለመፍታት በተወሰዱ እርምጃዎች አሁን ላይ በአመት 200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስጋ ማምረት መቻላቸውን አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ፕሬዝዳንት ኤልሳቤት ጌታሁን በበኩላቸው መንግስት በሎጂስቲክስ ዘርፉ ያደረገው ሪፎርም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡
በሪፎርሙ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚመቹ ህጎች መውጣታቸውንና የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችም በስፋት መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡
በተለይ በጉሙሩክ ዘርፍ በርካታ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማግኘት መጀመራቸውን አንስተዋል፡፡
የሎጂስቲክስ ዘርፉ መዘመን ላኪዎችና አስመጪዎች ያለምንም እንግልት በቀላሉ ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለይ አምራቾች የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳይገጥማቸው እድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የኢንቨስተሮች ማህበር ስራ አስኪያጅ ሕብረት ለማ ናቸው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025