
ቦንጋ፣ግንባት 1/2017 (ኢዜአ)፦የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓትን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ለማስፋት የኔትዎርክና የስልጠና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር በመተባበር በመንግስት የኤክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሄዷል።
በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ የኤክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት በ2014 ዓ.ም በዘጠኝ የፌዴራል ባለበጀት ተቋማት መጀመሩን አስታውሰው፥ ውጤታማነቱ ተረጋግጦ የማስፋት ስራ መጠናከሩን ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም በሁሉም የፌደራል ተቋማትና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ለማስፋት መቻሉንም ተናግረዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በክልሉ አብዛኛው የመንግስት ንብረት በግዢ መልክ የሚቀርብ መሆኑን አንስተው፥ በአግባቡ ለማስተዳደርና ብክነትን ለማስቀረት አሰራሩን ማዘመን ይገባል ብለዋል።
የኤክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት በክልሉ በግዥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን የሚፈታ በመሆኑ ክልሉ ያለውን አቅም ከግንዛቤ በማስገባት ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚሰራ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዘነ አዳሾ ገልፀዋል።
አሰራሩ አዲስ በመሆኑ በየደረጃው ላሉ ባለድርሻ አካላት ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ በበኩላቸው፣የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ይገጥሙ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በመፍታት ህግ እንዲከበር ይረዳል ብለዋል።
በዘርፉ የሚገጥሙ የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት ፍትሐዊነትንና እኩል ተወዳዳሪነትን የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የተመረጡ ተቋማት ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ያሉት ደግሞ የክልሉ መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺሀረግ ደበበ ናቸው።
የኤሌክትሮኒክስ ግዢ ሥርዓት በተጫራቾች አለመኖር የሚፈጠር የመዘግየት ችግርን እንዲሁም በሂደቱ ሊገጥሙ የሚችሉ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደሚፈታም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026