
አዳማ፤ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ለተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ውጤታማነት የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ሊጠናከር እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አስገነዘቡ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ምክትል ሰብሳቢዎች በፖሊሲው ላይ ተጨማሪ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ውይይት በአዳማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሎሚ በዶ፤ በ1994 ዓ.ም የተዘጋጀው ነባሩ ፖሊሲ ሀገሪቷ አሁን ያለችበትን የዕድገት ደረጃና የህዝብ ፍላጎት ያላመከለ መሆኑን አስታውሰዋል።
ፖሊሲው የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ሁኔታ በትክክል ያልፈተሸ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሎሚ አዲሱ ፖሊሲ እነዚህን ክፍተቶች የሚሞላ ዓለም የደረሰበትን የግብርናና ገጠር ልማት እሳቤዎችን ያካተተ እንደሆነም ገልጸዋል።
ፖሊሲው የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ፣ልማትና በዘላቂነት ለመጠቀም የሚያስችሉና ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚያግዙ ሀሳቦች የተካተቱበት መሆኑንም ተናግረዋል።
አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ምርትና ምርታማነትን መጨመር ብቻ ሳይሆን ገበያ ተኮርና በዓለም ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶች በብዛትና በጥራት እንዲመረቱ የተሻለ እድልን የሚፈጥር መሆኑንም አስረድተዋል።
በመሆኑም የዛሬው መድረክም የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የፖሊሲውን አቅጣጫ በመገንዘብ ድጋፍና ክትትል እንዲያጠናክሩ ለማስቻል ነው ብለዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ አዲሱ ፖሊሲ በሰብል፣ በእንስሳት፣ በተፈጥሮ ሀብት፣ በገበያ ተኮር ምርት ረገድ የነበሩ ውስንነቶችን የሚቀርፍ መሆኑን ተናግረዋል።
ፖሊሲው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርዓተ ምግብን እውን ለማድረግ እንዲሁም የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖሊሲውን ለማስፈጸም የውል እርሻ፣ የዘርና የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር አዋጆች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው፥ በተጨማሪም ደንቦችና የማስፈፀሚያ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ እየተገባ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026