አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ የኢንቨስትመንት መስኮች መከፈታቸው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ማስቻሉን ሚኒስትሮች ገለጹ።
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና የበርካታ ሀገራት ኢንቨስተሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፥ ኢትዮጵያ ሰፊ መሬት፣ ከፍተኛ የውሃ ሀብት፣ ወጣትና የተማረ የሰው ኃይል እንዲሁም የተሟላ መሰረተ ልማት ያላት ሀገር መሆኗ ለኢንቨስትመንት ምቹ አድርጓታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የተገበረችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ችግሮችን የሚፈቱ ሪፎርሞች ዘላቂ ሀገራዊ ዕድገትን የሚያመጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የሕግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲሁም የንግድና ኢንቨስትመንት ምህዳሩን የመክፈት እርምጃዎችም ትልቅ ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።
በተወሰዱ እርምጃዎች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው፥ የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት በማረጋገጥ ለኢንቨስተሮች ምቹ አቅም መፍጠሯን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ወደ ስራ መግባቱም ተወዳዳሪ እና በግሉ ዘርፍ የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አንስተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር ናት ብለዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የግሉ ዘርፍ ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን ያወሱት ሚኒስትሩ፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፖሊሲ ዕይታን በመቀየር የግሉ ዘርፍ ዋነኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ለበርካታ አስርት ዓመታት ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ ዘርፎች መከፈታቸውን በማንሳት፥ ለኢንቨስትመንት ምቹ ያልነበሩ ህግጋትና ፖሊሲዎች ተሻሽለዋል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን በተመጣጣኝ ዋጋ የምታቀርብ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፥ ይህም ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር)፥ በለውጡ ዓመታት መንግስት ለኢንቨስትመንት ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ውጤት መመዘገቡን ገልጸዋል።
ፎረሙ ትብብርን በማጠናከር የኢንቨስትመንት እድሎችን እንደሚያሰፋም ጨምረው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025