
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና የቻይናው የቤጂንግ የግብርና እና የደን ሳይንስ አካዳሚ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
የትብብር ስምምነቱን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ ፕ/ሮ) እና የቤጂንግ የግብርና እና ደን ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ው ባውክሲን ተፈራርመውታል።
የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ተመራማሪ ልዑካን ቡድን አባላት በተገኙበት በተደረገው ስምምነትም ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚቻልባቸው ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ሮ) በዚሁ ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ስምምነቱ ከዚህ ቀደም በቻይናው አካዳሚ በተደረገ የስራ ጉብኝት የተፈጠረ የመልካም ግንኙነት ትብብር ውጤት ነው።
ከቤጂንግ የግብርና እና ደን ሳይንስ አካዳሚ ጋር የተደረገው የትብብር ስምምነትም የኢትዮጵያን የግብርና ምርምር ስራን በላቀ የቴክኖሎጂ ምርምር ማስደገፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ቻይና የገነቡት ሁሉን አቀፍ የወንድማማችነት ትብብርም ከአካዳሚው ጋር በግብርና ምርምር ዘርፍ በትብብር መስራት የሚቻልበትን ስምምነት ማድረግ ያስቻለ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል።
የሁለቱ ተቋማት ስምምነቱም የጋራ ልምድና ተሞክሮን በመቀያየር በቴክኖሎጂና የምርምር ላብራቶሪ ግንባታ በትብብር መስራት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
በስምምነቱ መሰረትም የምርምር ተቋማቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ፣ በእንስሳት ሃብትና ሰብል ምርታማነት፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ የምርምር ስራ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።
የቤጂንግ የግብርና እና የደን ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ው ባውክሲን፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ስልጣኔ መነሻና በር ከፋች ነች ብለዋል።
የሁለቱ ተቋማት የትብብር ስምምነትም የኢትዮ-ቻይናን ወዳጅነት በግብርና ቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግርን በመፍጠር አጠናክሮ ለማስቀጠል ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የቤጂንግ የግብርና እና የደን ሳይንስ አካዳሚ የስራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን አባላት በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በቢሾፍቱ የግብርና ምርምር ማዕከል፣ በሆለታ የባዮ-ቴክኖሎጂ ምርምርና የግብርና ማዕከል የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026