
ባህር ዳር፤ ግንቦት 5/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት መንግስታዊ አገልግሎቶችን ይበልጥ ማቀላጠፍ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮውና የክልሉ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን በክላስተር ተቀናጅተው እያከናወኑት ያለውን ተግባር አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቤል ፈለቀ እንደገለጹት፤ የተቀላጠፈ መንግስታዊ አገልግሎት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ የዲጅታል ቴክኖሎጂን ማዘመንና መጠቀም ያስፈልጋል።
ለዚህም የክልሉን የቴክኖሎጂ ልማትና ፍላጎት ሊመልስ በሚችል አግባብ የለሙትንና እየለሙ ያሉ የዳታ ማዕከላት አቅም በማሻሻል ወደ አንድ ማዕከል የመረጃ ቋት የማስገባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እንዲሁም በኦን ላይን አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ሲስተሞችን በየዘርፉ በመለየት እያለሙ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በስማርት ሲቲ ፕሮጀክትም ስቹዌሽን ሩምና ስማርት ፖሎችን የማዘጋጀት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኃይል ቆጣቢና ሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲስተሞችን የማዘመን ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ሲስተሞቹ ለምተው ሲጠናቀቁ የመንግስትን የአስተዳደር ወጪ የሚቀንሱ፣ የተገልጋዩን እርካታ የሚጨምሩና ተጠያቂነትን በማስፈን የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችሉ ገልጸዋል።
የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት፣ የንግድና ገበያ ልማት፣ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ሌሎች ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማልማት የሚሰጡትን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግም ቢሮው እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎትን በጥራትና በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካም የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች በማስፋፋት ምቹ መደላድል መፍጠሩንም አስታውቀዋል።
የክልሉ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ያየህ በበኩላቸው፤ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፉን ለማዘመን ከማንዋል ወደ ዲጅታል አሰራር የመቀየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ስማርት ሲቲ ግንባታ በሚካሄድባቸው ከተሞች እየተከናወኑ ባሉ ሰፋፊ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለሞተር አልባ ትራንስፖርት መስፋፋት ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስንጠቀም ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ እደጋ ለመቀነስ ያስችላልም ነው ያሉት።
የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማዘመንና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አምስት የትራፊክ ኮምፕሌክሶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን በመጥቀስ ሌሎችም የተከናወኑ ተግባራትን አብራርተዋል።
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026