የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ዩኒቨርሲቲው የልማት ጥያቄዎችን ለሚመልሱ፣እድገትን ለሚያፋጥኑ የምርምር እና የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች ትኩረት ሰጥቷል

May 15, 2025

IDOPRESS

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 6/2017 (ኢዜአ)፡-የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለሚመልሱና እድገትን ለሚያፋጥኑ የምርምር እና የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች ትኩረት መስጠቱን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የማህብረሰብ ፎረም "ዩኒቨርሲቲው ከመማር መስተማር ባሻገር" በሚል ሃሳብ እየተካሄደ ነው።


በዚህን ጊዜ የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውድነህ ቶማስ (ዶ/ር) እንደገለጹት ተቋሙ የማህበረሰቡን የልማት ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙ ሥራዎች ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የልማት ግቦችን ለማሳካት ለምርምር እና ለማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች ልዩ ትኩረት መስጠቱን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ከ20 በላይ የምርምር ሥራዎችን ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መድቦ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ 63 የማህበረሰብ ጉድኝት እና ስምንት የቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክቶችን 38 ሚሊዮን ብር መድቦ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ፎረሙ ዩኒቨርሰቲው በአካባቢው የሚያካሂዳቸው የምርምርና ጥናት ሥራዎች የማህብረሰቡን ችግር ከመፍታትና ልማትን ከማፋጠን አንጻር በተጨባጭ ያመጡትን ውጤት ለመገምገምና ግብአት ለማሰባሰብ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምክትል ፕሬዚደንቱ አክለው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች እያካሄደ ያለውን ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል።


የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አክበር ጩፎ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል።

በተለይ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ባከናወናቸው ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን ነው የተናገሩት።


የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዳንኤል ዳሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በዞኑ ልማትን በማፋጠን የማህበረሰቡን ሀይወት ለመለወጥ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት አመስግነዋል።

በቀጣይም በሁለንተናዊ የልማት ሥራዎች የዩኒቨርሲቲው ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ገልጸው፣ የዞኑ አስተዳደር ለዩኒቨርሲቲው የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

በመድረኩ የዩኒቨርሰቲው አመራሮችና ተመራማሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲህም ከወላይታ ዞን የተለያዩ መዋቅር የመጡ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025