
አምቦ፤ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የጉደር - ጅማ አስፋልት መንገድ ግንባታ አካል የሆነውን የሰዮ-ሸነን-ጉደር መንገድ እየተፋጠነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለጸ።
ከአራት አመት በፊት የተጀመረው የአስፋልት መንገድ ግንባታ በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር ግንባታው መዘግየቱ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግንባታው ዳግም ተጀምሯል።
መንገዱ በአጠቃላይ 180 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰዮ-ሸነን-ጉደር 91 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታን እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነው።
በኮርፖሬሽኑ የሰዮ- ሸነን- ጉደር መንገድ ግንባታ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ደፈረ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአካባቢው በሰፈነው ሰላም የመንገድ ግንባታው በአዲስ መልክ ተጀምሮ በፍጥነት እየተከናወነ ነው።
መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ለሚደረግ ጉዞ አማራጭ መንገድ መሆኑን ጠቅሰው ግንባታውም በከተሞች 14 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በገጠር ደግሞ 10 ሜትር ስፋት እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህ ወቅትም የመንገዱን ግንባታ ፈጥኖ በማጠናቀቅ በመስመሩ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ አዳዲስ የግንባታ ማሽኖችን ወደ ስራ በማስገባትና ባለሃብቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎችን ባሳተፈ መልኩ ስራው እንዲፋጠን እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
የመንገዱ ግንባታ ለአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል ከመፍጠሩም ባለፈ ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

መንገዱ የሚያልፍበት የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት አስተዳዳር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ሂርኮ፤ በወረዳው ሰላም በመስፈኑ የመንገድ ስራው እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንገዱ ግንባታም የወረዳውን ልማት ለማፈጠን እንደሚያግዝ ጠቅሰው በተለይም ምርት ወደ ገበያ በወቅቱ ለማድረስና በወረዳው የባለሀብቶችን የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።
ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የጉደር ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው መንገዱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይዞላቸው የሚመጣ በመሆኑ የግንባታ ሂደቱ እንዲፋጠን የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የመንገዱ ግንባታ የከተማውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ መሆኑን አውስተው ግንባታው ፈጥኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የሰዮ - ሸነን- ጉደር - ጅማ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ እየተከናወነ እንደሚገኝም ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026