
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦ የብሪክስ አባል ሀገራት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ጥሪ አቀረቡ።
የብሪክስ የትራንስፖርት ሚኒስትሮች ስብሰባ በብራዚል መዲና ብራዚሊያ ተካሄዷል።
ኢትዮጵያ በስብሰባው ላይ በትራንስፖርት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ለውጦች አቅርባለች።
አዲስ ግዙፍ አየር ማረፊያ ግንባታ፣ የአየር ማረፊያዎች ማስፋፊያ እና የደረቅ ወደቦችን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን የማዘመን ግብ ያላቸው ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለማሳያነት ቀርበዋል።
በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል የመሆን ግብ እንዳላት ገልጸዋል።
አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት ከተቀረው ዓለም ጋር በማስተሳሰር እድገትን፣ትስስር እና ዘላቂነትን እውን ለማድረግ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
አምባሳደሩ የብሪክስ ሀገራት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትሮቹ ስብሰባውን ተከትሎ የጋራ አቋም መግለጫ ያወጡ ሲሆን ትራንስፖርት የእድገት እና ዘላቂ ልማት አሳላጭ እንደሆነ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026