ኢሉባቦር፤ግንቦት 7/2017 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል እየተተገበረ የሚገኘው የማር ምርት ኢኒሼቲቭ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች በጅማ፣ኢሉባቦርና ቡኖ በደሌ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በዚሁ ወቅት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቶሌራ ደበላ፣ የክልሉ መንግስት የጀመረው የማር ኢኒሼቲቭ ውጤታማ ሆኗል ብለዋል።
ኢኒሼቲቩ ከመጀመሩ በፊት ዓመታዊ የማር ምርት ከ45 ሺህ ቶን የማይበልጥ መሆኑን አንስተው፥ በአሁኑ ወቅት ከ117 ሺህ ቶን በላይ ማር ማምረት እንደተቻለ ተናግረዋል።
የነበረው የዘመናዊ ቀፎ ብዛት ከ7 ሺህ እንደማይበልጥ ገልጸው፥ በአሁኑ ወቅት ግን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዘመናዊ ቀፎ ለንብ አናቢዎች እንዲደርስ መደረጉን አስረድተዋል።
ለመጣው ውጤትም ዘመናዊ የንብ ማነቢያ ቀፎዎችን ለአርሶ አደሩ በስፋት ማቅረብ መቻሉና በንብ ማነብ ዙሪያ የተፈጠረው ግንዛቤ ማደግ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
በተለይም የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ለንብ ማነብ ስራ ምቹ በመሆናቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች በኢኒሼቲቪ ታግዘው ባከናወኑት ተግባር ምርቱ ከአገር አልፎ ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በአጠቃላይ በዚህ ወቅት በ15 የክልሉ ዞኖች የማር ምርት ኢኒሼቲቭ እየተተገበረ ሲሆን የዘርፉ ተጠቃሚነትም የበለጠ እንዲጎለብት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በኢሉአባቦር ዞን የያዮ እናት ንብ ማራቢያ ማእከል ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጉታ፤ ማዕከሉ የተሻሉ ዝርያ ያላቸውን ንቦች በማራባት ለንብ አናቢዎች በማከፋፈል ላይ ይገኛል ብለዋል።
በተጨማሪም ማዕከሉ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለሚገኙ ንብ አናቢዎች የክህሎት ሥልጠና በመስጠት የተጀመረውን የማር ኢንሼቲቭ ለማሳካት እየሠራ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዚሁ ዞን በንብ ማነብ ስራ ከተሰማሩት አርሶ አደሮች መካከል ጣሰው ልግዲ፤ ከመንግስት የዘመናዊ ቀፎ አቅርቦትና የክህሎት ስልጠና በማግኘታቸው ከዓመት ዓመት የማር ምርታቸው ጨምሯል።
አርሶ አደሩ በ34 ባህላዊ እና ከ200 በላይ ዘመናዊ ቀፎ ተጠቅሞ የንብ ማነብ ስራ እየሰራ ሲሆን በዚህ ዓመትም 400 ኪሎ ግራም ማር ማምረታቸውን ገልጸዋል።
ሌላው አርሶ አደር ተስፋሁን ጣሰው፤ በተመጣጣኝ ዋጋ መንግስት ያቀረበላቸውን ዘመናዊ ቀፎ ተጠቅመው ማር እያመረቱ እንደሆነ ተናግረው ተጠቃሚነታቸውም እያደገ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025