የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ የያዙ የተለያዩ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ሰጠ

May 16, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ የያዙ የተለያዩ መዝገቦችን መርምሮ ውሳኔ መስጠቱን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከታክስ እና ከጉምሩክ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የይግባኝ ቅሬታዎችን በህግና በአሰራር በመመርመር ውሳኔ ከመስጠት አኳያ፣ ውሳኔዎቹ የነበራቸው አፈጻጸምና ሌሎች ተያያዠ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ አያሌው፤ ከታክስ ከፋይ ማህበረሰብ እና ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን በታክስ አከፋፈል ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመመርመርና በማከራከር ፍትሀዊ ውሳኔዎችን ነጻና ገለልተኛ ሆኖ በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ውሳኔ ከተሰጠባቸው ውሳኔዎችም ከሶስት ቢሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ መጠን የያዘ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ከተሰጠው ውሳኔ መካከል ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት መዝገቦች ተሽረው ለግለሰቦቹ መወሰናቸውን አንስተው፤ ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት መዝገቦች በነበሩበት መጽናታቸውን ተናግረዋል፡፡

የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የውሳኔ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የኮሚሽኑን ውሳኔ ተከትሎ በይግባኝ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ መዝገቦች መኖራቸውን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ከሂደቱ መካከል ዘጠና አምስት በመቶ ኮሜሽኑ የወሰነውን ውሳኔ ያጸና እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

ይህም ኮሚሽኑ የሚሰጠው ውሳኔ ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ፤ ባለፉት ስድስት አመታት ወደ ስድስት ሺህ አምስት መቶ የሚጠጋ መዝገብ ውሳኔ መሰጠቱን ጠቅሰው፤ መዝገቡ ወደ ሀያ ሁለት ቢሊየን ብር የሚጠጋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በዚህም በ2018 በጀት ዓመት በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልሎች የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወኪል ለመክፈት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025