አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦ የእንስሳት ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ግብርና ሚኒስትር ገለጸ።
ግብርና ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን መመሪያ ላይ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ ውይይት ዛሬ ተካሂዷል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና በሽታን ለመከላከል የእንስሳት የጤና ኤክስቴንሽን ትግበራ ላይ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መጠናከር አለበት።
መንግስት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በነደፋቸው የተለያዩ ኢኒሼቲቮች አመርቂ ውጤቶች መገኘታቸውንም ተናግረዋል።
የእንስሳት ሃብት የሚፈለገውን ጥቅም እንዳይሰጥ ተግዳሮት ሆነው ከቆዩ ችግሮች መካከል የእንስሳት በሽታ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተዘጋጀው ኤክስቴንሽን ተግባራዊ መሆኑ በሽታን በመከላከል የሚገኘውን ፋይዳ እንደሚያሻሻል ጠቅሰዋል።
በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች የእንስሳት በሽታን በጋራ በመከላከል በኩል ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የተዘጋጀው ኤክስቴንሽን የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ግንዛቤ በማጠናከር ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን መከላከል ያስችላል ብለዋል።
በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ተወካይ ጌታቸው ጋሪ በበኩላቸው ኤክስቴንሽኑ የእንስሳት በሽታን ለመከላከል ከሚኒስቴሩ ጋር በመቀናጀት በትኩረት መስራት ያስችላል ብለዋል።
የዓለም አቀፍ እንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ተወካይ ዶክተር ከበደ አመኑ፤ በኢትዮጵያ በእንስሳት ልማት ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራትን በምርምር በመደገፍ በኩል ኢንስቲትዩቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት።
የኢትዮጵያ እንስሳት ሐኪሞች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር እንድሪያስ ዘውዱ ማህበሩ በእንስሳት ጤና ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ኤክስቴንሽኑ ዘርፉን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
የስፓና ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሃላፊ ዶክተር ሃና ዘውዱ ድርጅታቸው በእንስሳት ጤና ላይ የሚሰራ መሆኑን ተከትሎ የተዘጋጀው የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን መመሪያ ስራቸውን ማሳደግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025