አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ማንሳታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን አውስተዋል ነው ያለው።
እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” አይነት ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞችን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለችም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነ-ምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት አስምረውበታል ሲልም ጠቁሟል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025