የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የተጎዳ መሬት አገግሞ ጥቅም እንዲሰጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

May 19, 2025

IDOPRESS

ሀዋሳ ፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ)፡- የተጎዳ መሬትን ተንከባክቦ በማልማትና መልሶ እንዲያገግም በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አመለከቱ።


ሚኒስትሩን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የአጋር አካላት ተወካዮች በሲዳማ ክልል ያገገመ መሬት ያሉባቸው አካባቢዎችን ምልከታ አከናውነዋል።


የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት የተራቆተ አካባቢን በማልማት የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬና የምግብ ተክሎችን አልምቶ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ስኬት እያስመዘገቡ ነው።


ዛሬ ላይ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተከናወኑ ተግባራት ተጎድቶ የነበረ መሬት አገግሞ ጥቅም ላይ ውሎ ማየታቸውን ጠቅሰው በዚህም መደሰታቸውን ገልጸዋል።


ለዚህም እንደማሳያ በሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ ለዓመታት ተራቁቶ የነዋሪው ስጋት የነበረውን አካባቢ ማህበረሰቡ ከልሎ በተፋሰስ በማልማት ቡና፣ አቦካዶ፣ እንሰትና ሌሎች ተክሎችን አልምቶ ገቢ እያገኘበት መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።


የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፤ የአለም ባንክ በውሀ፣ በአካባቢ ጥበቃና በተፋሰስ ልማት ዙሪያ በክልሉ የሚከናወኑ ተግባራትን እያገዘ ይገኛል ብለዋል።


በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች 140 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻሉ 15 ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙና ለዚህ ማስፈጸሚያ የሚሆን 750 ሚሊዮን ብር በጀት እንደተመደበም ተናግረዋል።


የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ማምሩ ሞኬ በበኩላቸው፥ በክልሉ 366 ተፋሰሶችን በመለየት 205 ሺህ ሄክታር የተራቆተ መሬት መልሶ እንዲያገግም መደረጉን ተናግረዋል።


በዚህም 51 ሺህ አባላት ያሉት ከ300 በላይ ማህበራትን በማደራጀት በንብ ማነብና በሌሎች መስኮች ተሰማርተው ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።


በአለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር አና ዌለንስቲን እንዳሉት፥ የአለም ባንክ ከግብርናና ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በንጹህ ውሀ አቅርቦትና በተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።


በሲዳማ ክልል በሸበዲኖ ወረዳ ለረጅም ዓመታት ተራቁቶ ለጎርፍ አደጋ ያጋልጥ የነበረን አካባቢ ነዋሪዎቹ አልምተው አቦካዶ በማልማትና ንብ በማነብ ስራ ተሰማርተው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ማየታቸውን ተናግረዋል።


ዛሬ በሲዳማ ክልል አለታ ጩኮና ሸበዲኖ ወረዳዎች በአለም ባንክና አጋር አካላት ድጋፍ በተከናወኑ ተግባራት ምልከታ ላይ የግብርና ሚኒስቴርና የሲዳማ ክልል የስራ ኃላፊዎችና የአጋር አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...

Jul 27, 2026

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...

Jul 21, 2026

ከአፍሪካ ትልሞች ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...

Jun 27, 2026

በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት አውጥተዋል

ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...

Jun 26, 2026