
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 9/2017(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር እየተሳተፉ የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚነታቸው እያደገ መሆኑን ገለጹ።
በዞኑ የሊበን ወረዳ ነዋሪ አቶ ኑራ ሀብቻና ከሦስት ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በዶሮ እርባታ ስራ መሰማራታቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ6ሺህ በላይ የሥጋና የእንቁላል ዶሮዎችን በማርባት በየወሩ እስከ 3ሺህ እንቁላል ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሥራ ሲጀምሩ የነበራቸው 100ሺህ ብር ካፒታል በዚህ ወቅት ከ400ሺህ ብር በማለፉ በቀጣይ ወደ ንብ ማነብና የወተት ላም እርባታ ለመሸጋገር እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በነገሌ ቦረና ከተማ ዙሪያ ንብ በማናብ ሥራ የተሰማሩት አቶ ዘሪሁን በቀለ፤ 10 ዘመናዊ የንብ ቀፎ ተጠቅመው የንብ ማናብ ስራ መጀመራቸውን ጠቁመው ከ4ቱ ቀፎዎች ለመጀመሪያ ጊዜ 55 ኪሎ ግራም ማር ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ማንጎ፣ ሙዝና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን ማልማት መጀመራቸውን ገልጸው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።
የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪውና በአሣ እርባታ ሥራ የተሰማሩት አቶ በሽር ዱባ፤ የአሳ ምርት ለገቢያ በማቅረብ ቤተሰቦቻቸውን እያስተዳደሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወደ ፊትም ከአሣ እርባታ ስራ በሻገር በንብ ማነብ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በመሳተፍ ገቢያቸውን ለማሳደግ ማቀደቻውን ጠቁመዋል።
በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ጸጋዎች አጠቃቀም ባለሙያ አቶ በረከት ዳመነ እንዳሉት፤ በዞኑ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከ148 ሺህ በላይ ዜጎች እየተሳተፉ ነው።
በዚህም የአሳ ሀብት ልማት፣ የንብ፣ ዶሮ፣ የስጋና የወተት ላሞች እርባታ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው አትክልትና ፍራፍሬም እየተመረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
የሌማት ትርፋት መርሃ ግብር ምርታማነትን ለማሳደግ ከ1 ሚሊዮን በላይ የዶሮ ጫጩቶዎች፣ ከ13 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ለተጠቃሚዎች መከፋፈላቸውን አስታውቀዋል።
በተለይም የተሰራጨው ዘመናዊ ቀፎ ቀድሞ ከአንድ ባህላዊ ቀፎ የሚገኘውን 8 ኪሎ ግራም የማር ምርት ወደ 35 ኪሎ ግራም ማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሌማት ትሩፋት አምራቹንና ሸማቹን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ መሆኑንም አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026