ወራቤ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በምርምር፣ ፈጠራና በማህበረሰብ አገልግሎት እያገዙ መሆኑ ተገለጸ።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ 3ኛውን የምርምር ኮንፍረንስ “ፈጠራና ምርምር ለዘላቂ ልማትና ማህበራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሀሳብ እያካሄደ ነው።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በኮንፍረንሱ እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የክልሉ መንግስት እያከናወነ ያለውን የልማት ስራ በምርምርና በአዳዲስ ፈጠራዎች የሚያግዙ ተግበራት እያከናወኑ ነው።
ክልሉን የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል በማድረግ ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲቻል እየተሰራ ነው ያሉት አቶ አንተነህ ለዚህ ደግሞ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በክልሉ የሚገኙት ወራቤ፣ ዋቸሞና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በክልሉ እየተካሄደ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያገዙ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህም የመምህራንን አቅም በመገንባትና ለክልል አቀፍና ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶፊቅ ጀማል(ዶ/ር ኢ/ር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በመደበኛነት ከሚያከናውነው የመማር ማስተማር ስራ በተጓዳኝ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተግባራት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በግብርናው ዘርፍ የእንስሳትን ዝርያ በማሻሻልና ሀገር በቀል ዕውቀት ላይ በማተኮር የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቅሰዋል።
በስልጤ ዞን ግጭትን ቀድሞ መከላከል በሚያስችለው “ሴራ” በተሰኘው የባህል ዕሴትን በጥናት በማስደገፍ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መተግበር የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውንም ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አንዋር አህመድ በበኩላቸው በማህበረሰብ አገልግሎት የህዝብ መድሀኒት ቤት በመክፈት አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ተናግረዋል።
በትምህርቱ ዘርፍ አምና በክልሉ በ38 ትምህርት ቤቶች ለአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ከሁለት አመት በፊት ከነበረው አንጻር የተማሪዎች ውጤት መሻሻል እንዲያሳይ ማገዙን ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው በተያዘው ዓመትም ከ40 በሚበልጡ ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው 3ኛው የምርምር ኮንፍረንስ የተመረጡ 40 የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተመላክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025