
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2017(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ፖሊስ ውጤታማ የለውጥ ስራዎች ዓለም አቀፍ እውቅና እያስገኙ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ በዓለም አቀፍ የፖሊስ ጉባኤ ላይ ምርጥ የፖሊስ መተግበሪያ ተብሎ በአንደኝነት መሸለሙ ይታወቃል።
እንዲሁም ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል በተሰራው ውጤታማ ስራ የሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል።
ሽልማቶቹን በማስመልከት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የፌዴራል ፖሊስ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።
በፖሊስ ምርመራ እና ወንጀል መከላከል ላይ ያተኮሩ የሪፎርም ስራዎች መከናወናቸውን ለአብነት ጠቅሰው፤ በዚህም በቴክኖሎጂ በታገዘ ወንጀል መከላከል ስራ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
የፌዴራል ፖሊስ ውጤታማ የለውጥ ስራዎች ዓለም አቀፍ እውቅና እያስገኙ መሆኑን ጠቁመው ለአብነትም የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ምርጥ የፖሊስ መተግበሪያ ተብሎ መሸለሙን አንስተዋል።
ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል ዙሪያ በተሰራው ውጤታማ ስራም እውቅና መገኘቱን አመልክተዋል።
ፌዴራል ፖሊሲ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ውጤታማ የወንጀል መከላከል እና ዘመኑን የዋጀ የምርመራ ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በቅርቡም ስራውን የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎች ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጸዋል።
የፌዴራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደምሴ ይልማ በበኩላቸው፤ የፌዴራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ወንጀልን በመከላከል ባስገኘው ከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸዋል።
ሽልማቶቹ ፌዴራል ፖሊስ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ አኩሪ ውጤት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
ፖሊስ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በቀጣይም ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026