
ገንዳ ውሃ፤ግንቦት 16/20217 (ኢዜአ)፦በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም በመጠበቅ በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ የኢንቨስትመንት ስራዎችን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ በምእራብ ጎንደር ዞን በእርሻ ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶችና አርሶ አደሮች ገለጹ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በእርሻ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶችና አርሶ አደሮች ጋር የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሄዷል።
በመተማ ወረዳ ከዳስጉንዶ ቀበሌ የመጡት አርሶ አደር ሰኢድ ሙሀመድ በምክክሩ ላይ እንደገለጹት በአካባቢው የተፈጠረው የጸጥታ ችግር በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆኗል።
ሆኖም አሁን ላይ በአካባቢው በሰፈነው ሰላም ምክንያትም የጀመሩትን የልማት ስራ ለማስቀጠል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር የመጡት ባለሃብት አቶ ደሴ ሲሳይ በበኩላቸው በአካባቢው የሰፈነው ሰላም ወደ ልማት ለመግባት አመቺ መሆኑን ገልፀው የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
በእርሻ ኢንቨስትመንት ረገድ ያጋጠሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመንግስት ጎን በመቆም ለመፍታት የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ከመንግስት ጋር በመሆን በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም በመጠበቅና የህግ የበላይነት ስራዎች እንዲጠናከሩ አበክረው እንደሚሰሩ የገለፁት ደግሞ ሌላኛው ባለሃብት አቶ ሙሀመድ ካቲም ናቸው።
በሰላም ረገድ የተፈጠረውን ዕድል በመጠበቅ የጀመሩትን የእርሻ ኢንቨስትመንት ስራ ለማስቀጠል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑንም አክለዋል።
የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ዘውዱ ማለደ እንደገለጹት መንግስት በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየሰራ ይገኛል።
አካባቢው ሰፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት የሚካሄድበት የልማት ቀጠና ቢሆንም ባጋጠመ ወቅታዊ ምክንያት በስፊው መልማት አለመቻሉን ገልፀው ''ለሰላም መስፈን ቅድሚያ ሰጥተን ልንሰራ ይገባል'' ብለዋል።
በአካባቢው የህግ የበላይነትን ከማስከበር ጎን ለጎን በአርሶ አደሩና በባለሃብቱ የሚነሱ መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ክልሉ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በበኩላቸው አሁን ላይ የተገኘው ሰላም ከባለሃብቱና ከአርሶ አደሩ ጋር መነጋገር የሚያስችል እድል መፍጠሩን አስረድተዋል።
በቀጣይም መንግስት እያደረገ ያለውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ህዝቡም የፅንፈኝነት አስተሳሰብን በመቃወም የትግሉ አካል መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026