
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማን በልማት የማዘመንና የመለወጥ ተግባራት ነዋሪዎችን ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ የመከላከል አካል ሆኖ መታየት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ቀን "ከአደጋ ስጋት ለተጠበቀ ከተማ ልማት የሚከፈል መስዋዕትነት ጀግንነት ነው" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሯል።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)ን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ በከተማው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎችን መከላከል የሚያስችሉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።
በከተማው እየተከናወኑ ያሉ መሰረተ ልማቶች ከተማውን ከማስዋብ በላይ ህብረተሰቡን ከእሳትና ከሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል የሚያስችሉ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ወቅቱንና ዘመኑን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት እንዲችል መደረጉን ጠቁመው፤ በተለይ በሰው ሃይልና ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ የማደራጀት ስራ መከናወኑን አብራርተዋል።
የእሳትና አደጋ ሰራተኞች ለሚሰጡት የጀግንነት አገልግሎትም ከንቲባዋ አክብሮትና ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል እያደረገ ያለው ተግባርና ዝግጁነት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መንስኤዎችና ጥንቃቄ ዙሪያ ለህብረሰተቡ ግንዛቤ እየሰጠና አደጋዎች ሲከሰቱም ፈጥኖ የመከላከል ተግባር እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኮሪደር ልማቱ የመንገድ መጨናነቅ ችግርን እንደፈታ ጠቅሰው፤ ይህም የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የተከሰተበት ቦታ በፍጥነት ለመድረስ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ በተለያዩ ደረጃ ለሚገኙ 928 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች እንደየደረጃቸው ማዕረግ ተሰጥቷል።
ማዕረግ ከተሰጣቸው መካከል ሲስተር መቅደስ ብርሃኑ በአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቦሌ ቅርንጫፍ በቅድመ ሆስፒታል አምቡላንስ ላይ በነርስነት በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

በዚህም የሰውን ሕይወትና ንብረት መታደግ ተግባር ላይ መሰማራት ሰብዓዊነት ያለውና የሚያስደስት መሆኑን ገልጻለች።
በኮሚሽኑ የአምቡላንስ ካፕቴን እንዳለ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ የእሳትና አደጋ ስራ ተግባር ለህሊና ደስታ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።

እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ ተከብሯል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026