የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመዲናዋ የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በመክፈልና በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ ፕሮጀክቶችን በማሳለጥ በኩል አቅም ፈጥሯል

May 26, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በመክፈልና በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ አቅም መፍጠሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

’’የንግዱ ማህበረሰብ ሚና፤ ለሁለንተናዊ ብልጽግና’’ በሚል መሪ ሀሳብ የንግዱ ማህበረሰብ የምክክር መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።


የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የንግዱ ማህበረሰብ መድረክ በወረዳና ክፍለ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱንና ዛሬ የሚካሄደው በከተማ አስተዳደር ደረጃ ነው።

መድረኩ በመዲናዋ በትብብር የተገነቡ የልማት ስራዎችን በማየት በቀጣይ በዕቅድ የተያዙ የትኩረት መስኮች ላይ በመወያየት የጋራ ተሳትፎ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ላይ በንግዱ ማህበረሰብ የሚነሱ ጉዳዮች ተቀራርቦ መፍትሔ ለመስጠት ዕድል የሚፈጥር ምክክር መሆኑንም አስረድተዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ አዲስ አበባን ውብ ገጽታ ያላበሱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የጋራ ውጤቶች መሆናቸውን በመጥቀስ።

በመዲናዋ ለተገነቡ ፕሮጀክቶች ስኬት የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በመክፈልና በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ያደረገው የነቃ ተሳትፎ የልማት ስራን በማሳለጥ አቅምና ጉልበት እንደፈጠሩም አንስተዋል።

በመዲናዋ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማነት የንግዱ ማህበረሰብ አሻራ ጭምር በመሆናቸው ቃል በተግባር የታየባቸው መሆኑን በመድረኩ የተሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ ገልጸዋል።

በመዲናዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገነቡ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች አስደናቂ የልማት ስራዎች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በመዲናዋ የተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግብር ከፋዩ የሚከፍለው ገንዘብ ለምን ልማት እንደዋለ የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉም ነው የገለጹት።

በግብር አከፋፈል ስርዓት ላይ የሚስተዋሉ የኦዲትና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መፍትሔ መስጠት እንደሚያስፈልግም ጠይቀዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ እንዳሉት የመዲናዋን የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት የሚያሳልጡ ሕጋዊና ተቋማዊ የሪፎርም ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በመዲናዋ ግብር የመሰብሰብ አቅምን በከፍተኛ መጠን ማሳደግ መቻሉን ገልጸው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ 161 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚያጋጥሙትን የሌብነትና ብልሹ አሰራሮች በማረም ቀጣይነት ያለው ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት በመዲናዋ ለተገነቡ ፕሮጀክቶች ውጤታማነት የግብር ከፋዩ ሚና ከፍተኛ ነው።

በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል በተወሰደ ህጋዊ እርምጃ በአንድ ዓመት ብቻ 160 ሰዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን አውስተዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚያጋጥሙ ክፍተቶች ምላሽ ለመስጠት በተቋማት ላይ የሪፎርም ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025