የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በማእከላዊ ጎንደር ዞን ከሚገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል ስድስቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

May 28, 2025

IDOPRESS

ጎንደር፤ግንቦት 19/2017 (ኢዜአ)፦በማእከላዊ ጎንደር ዞን ከ240 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ ካሉት የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል ስድስቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች መምሪያ አስታወቀ፡፡


የመምሪያው ተወካይ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ፈለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት አርሶ አደሩ በመስኖ ጭምር ተጠቅሞ በምግብ ራሱን እንዲችል እየተሰራ ነው።


በዚህም በዞኑ የሰፈነው ሰላም የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ ከተጀመሩ 26 የመስኖ ፕሮጀክቶች ውስጥ አሁን ላይ ስድስቱን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል።


የተጠናቀቁት የመስኖ ፕሮጀክቶችም ከሁለት ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ከ500 ሄክታር በላይ መሬትን በማልማት ከራሳቸው አልፎ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።


በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡት ፕሮጀክቶች ከ1 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡


በዝናብ አጠር አካባቢዎች የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች የአርሶ አደሩን የምግብ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጡና በምግብ ሰብል ምርት ራስን ለመቻል ለሚደረገው እንቅስቃሴ ምቹ መደላድልን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡


ቀሪዎቹን ፕሮጀክቶች ፈጥኖ በማጠናቀቅ በቀጣዩ ዓመት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ተስፋሁን አስረድተዋል።


የአርሶ አደሩን ኑሮና ህይወት ለመቀየር የሚያግዙ የመስኖ ፕሮጀክቶች ደጃፋችን ላይ ተገንብተው በዓመት ሁለቴ አምርተን ለመጠቀም ችለናል ያሉት የምእራብ ደንቢያ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር የሻምበል የኋላሸት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025