
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የወደፊት የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆን የሚስችላትን መሠረት እየገነባች መሆኑን አሜሪካዊው የአፍሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን ገለጹ፡፡
ተንታኙ በኢትዮጵያ የሚገኙ የጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የብረታ ብረትና የስኳር ፋብሪካዎችንና ሌሎች የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ በአምራች ዘርፉ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ያሉ በርካታ የማኑፋክቸሪንግ ስራዎች እንዳሏት ያነሱት ተንታኙ በዘርፉ የጀመረችውን ሽግግር ይበልጥ ማፋጠን እንዳለባትም ገልጸዋል፡፡

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የወደፊት የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆን የሚስችላትን መሠረት እየገነባች ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አክለውም ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተመልክቻለሁ ነው ያሉት፡፡
እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ዛሬ ያሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቁመው፤ በኢትዮጵያ በአምራች ዘርፉ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026