
ጂንካ፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፦በጂንካ ከተማ በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የመዝናኛ ፓርክን ጨምሮ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስራ መከናወኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ ።
የጂንካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አሳየኝ በቀለ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በከተማው ነዋሪውን ያሳተፈ የኮሪደር ልማት ስራ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስራ ተከናውኗል።
''ጂንካን በጋራ እናልማ ''በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ ህዝባዊ ንቅናቄ ለኮሪደር ልማቱ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ገልፀዋል።
በዚህም የጂንካ ከተማን ገጽታ በመቀየር ሳቢና ምቹ ሊያደርጋት የሚችል የተቀናጀ የኮሪደር ልማት መሰራቱን ጠቅሰዋል።
ከተሰሩ ስራዎች መካከል ለበአላት ማክበሪያ እንዲሁም ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውል ፓርክ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የመንገድ አካፋይ፣ የመብራት ዝርጋታና የአደባባይ ልማትን ለአብነት አንስተዋል።
የመንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጨምሮ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስራ ተጠናቅቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ ልማቱ ለከተማዋ ልዩ ገጽታን ማላበሱን ተናግረዋል።
የከተማው ነዋሪ ልማቱን ለማሳለጥ የሚያደርገው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን አንስተው፥ የከተማ አስተዳደሩም ይህን አቅም በመጠቀም የበለጠ ለማልማት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በቀጣይም በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሦስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስራ ለማከናወን መታቀዱን አመልክተዋል።
በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ለከተማ ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት የከተማዋ ነዋሪ አቶ ከሊል ሙሐመድ፥ ዘገምተኛ ለነበረው የከተማዋ ዕድገት መፋጠን ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።
በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን እድገት አንድ እርምጃ ከፍ አድርጎታል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ትዕግሥት አድማሱ ናቸው።
ከዚህ ቀደም በቂ የእግረኛ መንገድ ባለመኖሩ የተሽከርካሪ አደጋ በስፋት ይከሰት እንደነበር አስታውሰው።
አሁን ላይ የእግረኛ መንገዶች ከተሰሩ በኃላ የተሽከርካሪ አደጋ መቀነሱን አንስተው፥ ከተማዋም ውብ፣ፅዱና ማራኪ እየሆነች መምጣቷን ተናግረዋል።
በከተማዋ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፥ እየተከናወነ ያለውን ተግባር በመደገፍ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026