ደብረ ማርቆስ፤ ግንቦት 23/2017(ኢዜአ)፡- የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ያመቻቸላቸው የስራ ዕድል እራሳቸውን በመቻል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው በከተማው በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣቶች ተናገሩ።
የአካባቢን ጸጋ በማልማት የስራ አጥነትን ለማቃለል በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ17ሺህ 600 በላይ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ስራና ስልጠና መምሪያ አስታውቋል።
ይህም ክንውን በበጀት ዓመቱ ከ20ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ከታቀደው ውስጥ እንደሆነ ተመልክቷል።
ከስራ እድሉ ተጠቃሚዎች መካከል የከተማው ነዋሪ ወጣት የሩቅሰው ታደለ ለኢዜአ በሰጠችው አስተያየት፤ በዚህ በጀት ዓመት ሦስት ሆነው በመደራጀት በዶሮ እርባታ መሰማራታቸውን ገልጻለች።
ወደ ስራው ሲገቡም መንግስት የመስሪያ ቦታ እና 250ሺህ ብር ብድር ማቅረቡን ተናግራለች።
በእስካሁኑም ለሦስት ጊዜ ያህል ጫጩት በማሳደግ ባከናወኑት ግብይት ከ110ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን አስረድታለች።
በዚህም ከስራቸው በሚያገኙት ገቢ ከቤተሰብ ጠባቂነት በመላቀቅ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው ጠቅሳለች።
ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት ዳዊት አትንኩት በበኩሉ፤ ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር አስታውሶ፤ በእንጨትና ብረታ ብረት ዘርፍ ተደራጅተው በመስራታቸው ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ ገልጿል።
አሁን ላይ ከመንግስት ባገኘው 100ሺህ ብር መነሻ ካፒታል በግሉ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።
የከተማ አስተዳደሩ ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ መኮነን ሙሉአዳም እንዳሉት፤ የአካባቢን ጸጋ በማልማት ስራ አጥነትን ለማቃለል እየተሰራ ነው።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ20ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለመፍጠር ከታቀደው ውስጥ በእስካሁኑ ከ17ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።
በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በሌሎችም ዘርፎች የስራ እድሉ የተፈጠረ ሲሆን፤ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ብድርና ከ70 በላይ ሼዶች ተመቻችቷል ሲሉ ገልጸዋል።
እቅዱን ለማሳካት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የስራ ዕድል ፈጠራውን በማስፋፋት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025