ድሬደዋ፣ግንቦት 24/2017(ኢዜአ )፦የሎጂስቲክስ ዘርፉን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የአሽከርካሪዎች ሚና የላቀ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ ተናገሩ።
የሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ለአሽከርካሪዎች በድሬደዋ ተሰጥቷል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የተጣለባቸውን አገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት እያከናወኑ ለሚገኙት ተግባራት ምስጋና ይገባቸዋል።
የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሀገርን አደራ ተሸክመው በሚያከናወኑት ስራ ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህን ጥረታቸውን ከአደጋ በመጠበቅ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።
ተልዕኳቸውን በላቀ ደረጃ ለማሳደግና የሎጂስቲክስ ዘርፉን ቀልጣፋና ፈጣን እንዲሆን የተለያዩ የማሻሻያ አሰራሮች ተዘርግተው በመተግበር ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በተለይም የተጀመረውን የአሰራር ለውጥ በተቀናጀ መንገድ በመተግበር የወጪና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የአሽከርካሪዎች ሚና ጉልህ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በመሆኑም የሎጀስቲክስ ዘርፍ አካል ለሆነው በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩት የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ባለድርሻዎች በድሬዳዋ የተዘጋጀው ስልጠና ተልዕኮን በፍጥነትና በጥራት ዳር ለማድረስ እንደሚያግዝም አስታውቀዋል።
በድሬደዋ የተዘጋጀው ስልጠና የሎጂስቲክስ ዘርፍን ለማሳደግ መሠረታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሽኩሪ አብዱረህማን ናቸው።
በከባድና አስቸጋሪ መልክዓምድር በመጓጓዝ ለሀገርና ለህዝብ ከፍታ እንዲሁም የተጀመረውን አገራዊ የለውጥ ዕውን ለማድረግ እየተጋችሁ ያላችሁ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባችኋሃል ብለዋል።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉት የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ በበኩላቸው፥ በድሬደዋ እና በአካባቢው አደጋን በመከላከል እና ጠንቅቆ በማሽከርከር በአብነት የሚጠቀሱት የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መሆናቸውን አንስተዋል።
ትናንት በተጀመረው ስልጠና ላይ የተሳተፉት የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው፥ በሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪ የአሽከርካሪዎች ሚና፣ የአሽከርካሪዎች ስነ ባህሪና አደጋ ተከላክሎ የማሽከርከር እንዲሁም በአደጋ ጊዜ ምላሾች ላይ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025