አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በብዙ አምርታ ለገበያ የምታቀርብ በትንሹ ደግሞ የምትሸምት ሀገር እንድትሆን እየሠራን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በተካሄደው የ3ኛው “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ አካል የሆነ ኤክስፖ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
በንግግራቸውም ጎንደር የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሥልጣኔ መገናኛ ከመሆኗም በላይ የአምራች ኢንዱስትሪ ኮሪደር እየሆነች መምጣቷን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የማንሰራራት ጉዟችን አንዱ ምልክት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በብዙ አምርታ ለገበያ የምታቀርብ በትንሹ ደግሞ የምትሸምት እንድትሆን እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል በችግር ጊዜም ቢሆን ሰላምን እያሰፈነ የልማት አርበኛ ሆኖ መቀጠል የመቻሉ ህያው ምስክር መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ታጥቀው የገቡ ልጆቿ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እየመጡ ወደ ማህበረሰባቸው እየተቀላቀሉ እንደሚገኙም አንስተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎንደር እንደ አዲስ እየተወለደች፣ እንደ አዲስ እየተሠራች እንዲሁም እየፈካች መሆኑንም ተናግረዋል።
መንግሥት ለሰላም እንዲሁም አምራች ኢንዱስትሪውን ጨምሮ ለልማት የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025