
ሆሳዕና፤ግንቦት 27/2017 (ኢዜአ)፦በበጀት ዓመቱ አሥር ወራት በሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሚኒስቴሩ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣በበጀት ዓመቱ ዜጎችን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል።
ባለፉት አስር ወራትም በሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ቋሚ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የሥራ ዕድሉ በግብርና፣በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ለክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው፣ በተከናወነው የሪፎርም ሥራም ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ኢኮኖሚው የሚፈለገውን የሰው ኃይል ለማፍራት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የየአካባቢያቸውን ጸጋ መሰረት ያደረጉ አጫጭር ስልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ዜጎች በቂ እውቀትና ሙያ አግኝተው እንዲወጡ ከማድረግ ባለፈ በሰለጠኑበት ዘርፍ የሥራ እድል እንዲያገኙም ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑንም ጠቅስዋል፡፡
የሚፈጠረው የሥራ ዕድል ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተሳሰረ መሆን እንዳለበት የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፥በአምስቱ የኢኮኖሚ አውታሮች ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ለዚህም ስኬት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአካባቢያቸውን ፀጋ ማዕከል ያደረገ ክህሎት መር ስልጠና እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሀዲያ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊራንሶ በበኩላቸው፥ በዞኑ ባለፉት 10 ወራት ለ88 ሺህ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በየአካባቢው ያለውን ፀጋ መሰረት ያደረገ ክህሎት መር ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወጣቶች በከተማና በገጠር ግብርና፣በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ እንዲሰማሩ መደረጉን ተናግረዋል።
በሆሳዕና ከተማ የውሃ ልማት ቴራዞና ብሎኬት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ ሰብሳቢ ወጣት በለጠ ደገፈ እንደገለፀው፣ በበጀት ዓመቱ በ10 ሰዎች በመደራጀት ከመንግስት በብድር ባገኙት 1 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር ካፒታል ሥራ ጀምረዋል፡፡

በዚህም ከራሳቸው ባለፈ ለ45 ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፍጠራቸውን ጠቁሞ፣ ሰርተው በሚያገኙት ገቢ ከመንግስት የወሰዱትን ብድር ከመመለስ ባለፈ ቁጠባ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢንተርፕራይዙ የሥራ ዕድል የተፈጠረላት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተመራቂዋ ወጣት ገነት ወንድሙ በበኩሏ፥መንግስት ወጣቶች ወደስራ እንዲገቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያደረገ መሆኑን ጠቅሳ፣ በተፈጠረላት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆኗን ተናግራለች።

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026