ድሬደዋ፣ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፡-የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ውበትና ገፅታ እያጎላና ፤የስራና የማህበራዊ አገልግሎት ችግሮችን እየፈታ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የድሬደዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በድሬደዋ በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተገነባ የሚገኘው 12 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የድሬደዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ ደረጃውን ጠብቆ በተለያዩ የከተማው አቅጣጫዎች የተገነባው የኮሪደር ልማት ድሬዳዋን ውብና ማራኪ የስራና የመኖሪያ ማዕከል አድርጓታል።
ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ፍቃዱ አበበ እንደገለፁት፤ የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ የተሽከርካሪዎችና የብስክሌት መንገዶች የፈጠረና ማህበራዊ ችግሮችን ያቃለለ ትልቅ ልማት ነው።
አቶ ታደለ ወልዴ በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ ከራሳቸው ጀምሮ ለብዙ ነዋሪዎች የስራ እድል ከመፍጠር በዘለለ የከተማውን ገፅታ በላቀ ደረጃ እየለወጠው ነው ብለዋል።
በልማቱ በፍጥነትና በጥራት ወደ ልዩ ውበት የቀየረና የነዋሪዎች መዝናኛ ስፍራ እየሆነ መምጣቱን የገለፁት ደግሞ ወይዘሮ ዘበናይ ተሰማ ናቸው።
በተለይም የነገ አገር ተረካቢ ህፃናት ከየአቅጣጫው ተሰባሰበው በአንድነት የሚዝናኑበት ስፍራ መሆኑ የልጆችን ፍቅር እና አንድነት የሚያጠናክር ይሆናል ብለዋል።
ከባሌ ሮቤ እንደመጣ የተናገረው ወጣት አብደላ ዑመር የኮሪደር ልማቱ ድሬዳዋን ይበልጥ ውብና ማራኪ ከተማ እንዳደረጋት ገልፅዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው የተሰሩትን ልማቶች በተናጠልና በተቀናጀ መንገድ በመንከባከብ ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ከማድረግ በተጨማሪ በምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል ።
በከተማው አምስት አቅጣጫዎች የተጀመረው 12 ኪሎ ሜትር የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የተሽከርካሪ ፣ የብስክሌት ፣ የእግረኛ መንገዶችን በውስጡ ያካተተ ሲሆን አሁን ላይ ልማቱ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑም ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025