አዲስ አበባ፤ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና ኬኒያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአህጉራዊ ርዕይ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣልን (ኢጋድ) አስተባባሪነት በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል በአፍሪካ ቀንድ የሁለትዮሽ ትብብር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ፤ የኬኒያ ብሔራዊ ግምጃ ቤት የኢንቨስትመንትና የንብረት አስተዳደር ሲሪል ኦዴዴ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማም የኢትዮ-ኬንያን የመሠረተ ልማት ትስስርን በማሳደግ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣በንግድና ድንበር ተሻጋሪ ልማት ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ነው።
የኬንያ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የፕሮግራሞች እና ደረጃዎች ዳይሬክተር ቶማስ ብዋሊ በውይይቱ ወቅት፥አገራቱ የተስማሙባቸውን ጉዳዮች አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ውይይቱ ድንበር ተሻጋሪ ትብብር፣ የንግድ ማመቻቸት እና ተግዳሮቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የጋራ ቁርጠኝነትን በድጋሚ አረጋግጠዋል ብለዋል።
የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብቶችን ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማዋል የሀብት ማሰባሰብ እቅድን ለማደስ መስማማታቸውን ጠቁመዋል።
ለቀጣናዊ ውህደት የጋራ ቁርጠኝነት እና ቀጣይነት ያለው ሰላም፣ ትስስር እና ሁሉን አቀፍ ልማትን ለማስቀጠል በጋራ ኃላፊነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ልማት ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ-ኬንያ ድንበር ላይ የሸቀጦችን፣ የሰዎችን እና የዲጂታል አገልግሎቶችን እንቅስቃሴ ለማሻሻል የለውጥ ፕሮግራም መሆኑ መመላከቱን ጠቁመዋል።
እንዲሁም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብቶችን ለህብረተሰባችን የጋራ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማዋል የግብዓት ማሰባሰብያ እቅድን ማነቃቃት የሚያስችል ምክክር በድጋሚ እንዲቀጥል ስብሰባው ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ልማት ተነሳሽነት በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር ላይ የሸቀጦችን፣ የሰዎችንና የዲጂታል አገልግሎቶችን እንቅስቃሴ የማሻሻል መርሃ ግብሮች እንዲካሄዱ ውሳኔ መተላለፉን ተናግረዋል።
አገራቱ ድንበር ተሻጋሪ የፋይበር ኦፕቲክ ግንኙነትን ለማጠናቀቅ፣ ድንበር ዘለል ዲጂታል አገልግሎቶችን ለማሻሻል፣የዲጂታል ስራዎችን ተደራሽነት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል ቁርጠኛ መሆናቸውን በውይይቱ ማረጋገጣቸውን አመላክተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025