ጋምቤላ፣ግንቦት 30/2017 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል በመኸር ወቅት ለማልማት ከታቀደው ከ88 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ቀድመው በሚዘሩ የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ በመኸር ወቅት ግብርና የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችንና የኩታ-ገጠም እርሻን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ፓል ቱት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ የግብርናውን ልማት በማጠናከርና በማዘመን ምርታማነትን በማሳደግ እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የታለመውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው።
በክልሉ በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ172 ሺህ 230 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብልና የጓሮ አትክልቶች በማልማት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በእስካሁኑ የመኸር እርሻ እንቅስቃሴም ለማልማት ከታቀደው መሬት ከ88 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው ቀድመው በሚዘሩ የበቆሎ፣የሰሊጥ፣ የለውዝና ሌሎች የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸዋል።
በተለይም በዘንድሮው ዓመት አርሶና አርብቶ አደሩን እንዲሁም ከባለሃብቱ ጋር በማቀናጀት የአፈር ማዳበሪያ ግብዓትን ተጠቅመው ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
በተጨማሪም የአርሶና አርብቶ አደሩን አደረጃጀት በማጠናከር የኩታ ገጠም እርሻ ስራዎችን በማስፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝም ኃላፊው ተናግረዋል።
በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት የታቀደው መሬት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም በ6 ሺህ፣ለመሰብሰብ ከታቀደው ምርት መጠን ደግሞ በ600 ሺህ ኩንታል ብልጫ እንዳለውም ተመላክቷል።
በአበቦ ወረዳ የዋንካክ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ኡጆዎ ኡጁሉ በሰጡት አስተያየት፥ የዘንድሮው የመኸር እርሻ አጋጥሞ ከነበረው መጠነኛ የዝናብ መቆራረጥ በስተቀር በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዘንደሮው የመኸር እርሻ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ በመግባት ቀድመው የሚዘሩ ሰብሎችን መዝራታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የዚሁ ወረዳ የመንደር ዘጠኝ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አዲሱ ብሩቃ ናቸው።
በቀጣይ ጊዜም የሩዝ ፣የማሽላ፣የማሾና ሌሎች ሰብል ዓይነቶች የሚዘራበት በመሆኑ ቀሪ ማሳቸውን በተጠቀሱት የሰብል ዓይነቶች ለመሸፈን እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025