አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በልማት ስራዎች ሴቶችን በሁለንተናዊ ዘርፉ ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ከከተማ አስተዳደሩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ሴቶች ጋር "የሴቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አካሂደዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማዋ በሚከናወኑ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ሴቶች በዕድገትና ሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና ጉልህ ነው።
ባለፉት አመታት የሀገርንና የከተማዋን ሰላም በማጽናት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስታውሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጥፋት ሃይሎችን አጀንዳ ቀድሞ በመረዳት ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸውም ከንቲባዋ አስገንዝበዋል።
በአዲስ አበባ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስራ ዕድል ፈጠራና በሌሎች ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ገልጸዋል።
በጤና፣ በትምህርት ቤት ምገባ፣ በቤት አቅርቦት፣ የኑሮ ውድነት ጫናን የሚያቃልሉ አማራጮችን በመተግበር በምግብ ዋስትና እና በሌሎች ዘርፎች ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ነው ያብራሩት።
በጤናው ዘርፍ ከተማ አስተዳደሩ ለጤና መድህን አገልግሎት ከፍተኛ ድጎማ ማድረጉን የገለጹት ከንቲባ አዳነች፤ በዚህም የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በቀጣይም በሁለንተናዊ መስክ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ ሴቶች ለዕድገትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ አስተዋጿቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ሴቶች በበኩላቸው በከተማዋ በሚከናወኑ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።
በዚህም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በተማሪዎች ምገባ፣ በጤናና በሌሎች ተግባራት ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ትኩረት መሰጠት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች ለከተማ አስተዳደሩ አቅርበዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የቤት አቅርቦት፣ ሴቶች ተደራጅተው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ማዕከላት ማስፋትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ቆንጂት ደበላ ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ከመድረኩ ሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችም በየደረጃው እየተፈቱ እንዲሄዱ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በቅዳሜ እና ዕሁድ ገበያ ምርት በተመጣጠነ ዋጋ በማቅረብ፣ በከተማ ግብርናና ሌሎች መርሃ ግብሮች ጫናውን ለማቃለል እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ዘርዝረዋል።
የእንጀራ መጋገሪያ ማዕከላትን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የማስፋፋት፣ የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ ፕሮጀክቶችን የመተግበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
በስራ ዕድል ፈጠራ ከወረዳ ጀምሮ ዲጂታል በሆነ መንገድ መረጃ በማጥራት ሴቶችን ቅድሚያ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025