አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2017(ኢዜአ)፦ከአገራዊ ለውጡ በኋላ ለክልሎች የሚተላለፈው የጋራ ገቢዎች የበጀት ሥርጭትን ፍትሃዊ ለማድረግ በተሰራ ሥራ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለፁ።
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተዘጋጀው ውስን ዓላማ ባላቸው የድጎማ በጀቶች ትልልፍና በጋራ ገቢዎች ክፍፍል ላይ ያተኮረ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና ሚኒስትሮች ታድመዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በውይይቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፣ ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በክልሎች መካከል ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በዚህም ከአገራዊ ለውጡ በፊት አራት ቢሊዮን ብር የነበረው የክልሎች የጋራ ገቢ የበጀት ክፍፍል አሁን ላይ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አንስተዋል።
የድጎማ በጀት ስርጭትን ግልፅና ፍትሃዊ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች መሰራታቸውንና በዚህም ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን አብራርተዋል።
በውስን ዓላማ ባላቸው ድጎማዎች የአሰራር ግልፀኝነትና የአተገባበር ክፍተት ላይ የሚነሱ ውስንነቶችን ለመፍታትም የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን አመልክተዋል።
የክልል መንግስታት ከፌዴራል መንግስት ስለሚደረግላቸው ድጎማ ለሚመለከታቸው ተቋማት በግልፅ ማሳወቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በመድረኩ በውስን ዓላማ የድጎማ በጀቶች ትልልፍ እንዲሁም በከፍተኛ ማዕድን አምራች ድርጅቶች የሚገኙ የሮያሊቲ ገቢዎች ክፍፍል ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን አስመልክቶ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025