
ወራቤ፤ ሰኔ 2/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተግባራዊ የሚደረጉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የአካባቢን ብክለት መከላከልን ማዕከል እንዲያደርጉ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡
ቢሮው ከክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በክልሉ የሚገኙ ፋብሪካዎችና የልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢ ብክለት ተፅዕኖን ለመከላከል ያለመ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ አካሂዷል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አብርሃም መጫ በወቅቱ እንዳሉት ቢሮው የተፈጥሮ ሀብትን በመንከባከብ ፅዱ አካባቢን ለመፍጠር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም የክልሉ ከተሞችን ፅዱና የአካባቢ ብክለትን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ ሀገር በቀል ችግኞችን እየተከሉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ አካላት የአካባቢን ብክለት መከላከልን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደምሰው ባቾሬ በበኩላቸው በአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚከሰትን ሁለንተናዊ ጫና ለመከላከል በኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማረም ቢሮው በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም ለአዳዲስ ኢንቨስትመንቶች የአካባቢ ብክለትን መከላከል በሚያስችል መልኩ በክላስተር መሬት የማዘጋጀት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በዞኑ የሚከናወን የትኛውም የልማት ስራ የአካባቢንና የማህበረሰቡን ጤና ማስጠበቅን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት ደግሞ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዘይኔ ቢልካ ናቸው፡፡
ዞኑን የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማዕከል ለማድረግ በተሰጠው ትኩረት በርካታ ባለሀብቶች ዘርፉን እየተቀላቀሉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የደስታ ጋርመንት ዋና ስራ አስኪያጅ ያሬድ ወልዴ በበኩላቸው ከፋብሪካው የሚወገዱ ተረፈ ምርቶች አካባቢን እንዳይበክሉ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በተለያየ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች የተሳተፉ ሲሆን የፅዳት ዘመቻና የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም አከናውነዋል፡፡
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026