
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦በመዲናዋ የተገነቡ ሁለገብ የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ አስተዋጽዎ እያበረከቱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) የላፍቶ ቁጥር ሁለት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ዛሬ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የገበያ ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን እንደ ድልድይ ሆኖ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ዛሬ የተመረቀው የላፍቶ ቁጥር 2 የገበያ ማዕከልም አምራቹንና ሸማቹ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የገበያ መሰረተ ልማቶችን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።

እንደሀገር መንግስት የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎችን በማስፋት ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ የንግድ ስርዓት ማሻሻል ለዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ መንግስት በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን መሰል የገበያ ማእከሎች የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት በኩል አይነተኛ ሚና እንዳለቸው አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሃቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፤ በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች የተገነቡት የገበያ ማእከላት በርካታ ጥቅሞችን ለነዋሪው እና ለአምራቹም ጭምር እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የተገነቡት ማእከላት አምራችና ሸማቹን በቀጥታ እንዲገበያዩ በማስቻል በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከቱ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሃብተማሪያም በበኩላቸው፤ ማዕከሉ አገልግሎት እንዲሰጥ የታሰበውን ዘመናዊና የተደራጀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ በርካታ መሰረተ ልማት የተሟሉለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የላፍቶ ቁጥር 2 የምርት ግብይት ማዕከልም በ8 ነጥብ 8 ሄክታር ላይ የተገነባ፣ 159 ሰፋፊና ምቹ ሱቆችን፣ 9 የጅምላ ማከፋፊያዎች እና 2 ሞሎችን የያዘ ነው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026