አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦ የንግዱ ማህበረሰብ የትናንት ስብራቷ የተጠገነ እና ነገዋ የተሰራ ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ስራ ላይ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገበያ እና ንግድ ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ገበያ ሀገር ይገነባል፣ ገበያ እውቀት ያሸጋግራል፣ ገበያ ስልጣኔ ያመጣል እንዲሁም ገበያ የአኗኗር ዘይቤን ይቀይራል ብለዋል።
ገበያ ብር የሚገኝበት ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር የሚገነባበት እና ለአንድ ሀገር ህልውና ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ረገድም የንግዱ ማህበረሰብ ካለው ሰፊ ተደራሽነት አንጻር በሀገር ግንባታ እና እድገት ላይ ጉልህ ድርሻ አለው ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ የከረሙ እና አዲስ ፈተናዎች ያለባት ሀገር መሆኗን ገልጸው የከረሙ ፈተናዎች ፈትቶ የወደፊቱ ላይ መስራት ካልተቻለ ትውልድ የተጠገነ ትናትና ያልተሰራ ነገን ስለሚረከብ መከራው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ያለፈውን መጠገንና የመጪውን የመሽቀዳደም ዘመን ሚዛን ጠብቆ መሄድን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚገባም ነው ያስረዱት።
ኢትዮጵያውያን ከዕለት ጉዳዮቻችን ባለፈ በዋና ሀገራዊ ጉዳዮችና ፈተናዎቻችን ላይ የመምከር ባህላችን መሻሻል እንደሚያስፈልገውም አንስተዋል።
በነገ የሀገር እጣ ፈንታ ያለመምከር ችግር በሁሉም ዘርፍ የሚታይ ጉዳይ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የንግዱ ማህበረሰብ ባለው ሰፊ አቅም እና ተደራሽነት ያለፉ ችግሮችን የመፍታትና ነገን የመገንባት ስራ ላይ ማህበረሰቡን የማስተማርና የማንቃት ላይ ስራ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025