
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች በአይነትም በመጠን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ገለጹ።
አራተኛው የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚና ንግድ ኤክስፖ በቻይና ቻንግሻ ከተማ ዛሬ ተከፍቷል።
ከኤክስፖው ጎን ለጎንም የኢትዮጵያን የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት በቻይና ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።
ስምምነቱን በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበውና የቻይና የጉምሩክ አጠቃላይ አስተዳደር ምክትል ሚኒስትር ዋንግ ልንግጁን ተፈራርመውታል።
አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ አዲስ የገበያ እድል ከማስገኘቱ በተጨማሪ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶችን መጠን ከፍ የሚያደርግ ነው።
ስምምነቱ ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ የግብርና ባለስልጣንና በቻይና ጉምሩክ ባለስልጣን በጋራ ሲዘጋጅ መቆየቱን አንስተዋል።
ስምምነቱ ከሀገሪቱ ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልጸው፤ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች በአይነትም በመጠንም ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በተመሳሳይም አምባሳደር ተፈራ 'ከቻንግሻ ሳተርንበርድ ኮፊ ኤልቲዲ' (Changsha Saturnbird Coffee Co.,LTD.) መስራች እና ሊቀመንበር ሚስተር ው ጁን ጋር የኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምሮ ለቻይና ገበያ ለማቅረብ እንዲችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ኩባንያው የኢትዮጵያ ቡናን በብዛት በመግዛት ለሌሎች የቻይና ቡና ኩባንያዎች ለማከፋፈል፣ ቆልቶ ለማዘጋጀት፣ለመፍጨት እና የቡና ምርቶች ለማዘጋጀት እንደግብዓት የሚጠቀም መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026