የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ መደላድል እየፈጠረ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ መደላድል እየፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 26 ለሚሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ አስረክበዋል።


የመስሪያ ቦታ ከተሰጣቸው መካከል 15ቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች አዲስ የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተሰጣቸው ናቸው።

በዚህ ወቅት ከንቲባ አዳነች መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚፈለገው ልክ አቅማቸውን ተጠቅመው ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ መደላድል የመፍጠር ስራ በትኩረት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የዘርፉ ተዋናዮች ከሚያነሷቸው አንኳር ጥያቄዎች መካከል የመስሪያ ቦታ መሆኑን አንስተው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች አግባብነትን ከተማ አስተዳደሩ በመፈተሽ ደረጃ በደረጃ መፍትሄ እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዛሬው ዕለትም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው የመስሪያ ቦታ ርክክብ አንዱ ማሳያ መሆኑን በመጠቆም።

እንደ ሀገር ትልቁ የእድገታችን ማነቆ ድህነት መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ለመፍታት አምራች ኢንዱስትሪዎች ያላቸውን እምቅ ሀብትና ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ከተማ አስተዳደሩም በቀጣይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚያመርቱት ምርት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ውስን ሀብት የሆነውን መሬት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ ነው ብለዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታን ፍላጎት መመለስ በሚያስችል አግባብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ይህን ፍላጎት ለመሙላት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በዛሬው እለት አዲስ የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተረከቡት መላ ፎር ኸር የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ማምረቻ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኤርሚያስ ሲሳይ በበኩላቸው፤ ምርታቸውን በተረጋጋ የመስሪያ ቦታ ለማምረት አቅም እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የሰጣቸው የመስሪያ ቦታ ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነታቸውን የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸው፤ ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ቁርጠኛ ነን ሲሉ አክለዋል።

የመስሪያ ቦታ ቁልፍ በመረከባቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለስራቸው የሚረዱ አዳዲስ ማሽነሪዎችን በማስገባት ተኪ ምርቶችን በስፋት ለማምረት ያግዘናል ያሉት ደግሞ የብራዘርስ ጋርመንት ስራ አስኪያጅ ነጻነት መቻል ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025