
አዲስ አበባ፤ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ብሄራዊ የትግበራ ስትራቴጂ አህጉራዊ ውህደትን ለማፋጠንና ሁሉን አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴን ለማራመድ ግልጽ ፍኖተ ካርታን ያስቀመጠ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን መተግበር የሚያስችላትን ብሄራዊ የትግበራ ስትራቴጂ ሰነድ አዘጋጅታለች።
ሰነዱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩትና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በሰነዱ ላይ የመጨረሻ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደት እውን መሆን የድርሻዋን እየተወጣች ነው።
ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግም የስትራቴጂው መዘጋጀት ትልቅ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ከፈረመች ጀምሮ ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስራዎችን ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰው፣የስትራቴጂው ዋና ዓላማዎች የአገርን ጥቅም የሚያስጠብቁና የገበያ ዕድሎችን የሚያሰፉ ናቸው ብለዋል።
ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ የንግድ ዘርፎች መከፈታቸውን ተከትሎ ምቹ የንግድና ኢንቨስትመነት ከባቢ መፈጠራቸውንም አንስተዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለአካባቢያዊና አህጉራዊ ውህደት ጠንካራ አቋም አላት ብለዋል።
ኢትዮጵያ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱን ካጸደቁ አገራት ቀዳሚ መሆኗን ገልጸው፤ ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል።
በዚህም ብሄራዊ አስተግባሪ ኮሚቴ መቋቋሙንና ስምምነቱ የሚመራበት ስትራቴጂክ ዘነድ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
አስተማማኝና ተገማች ገበያ ለአገር ምጣኔ ሃብት ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ኢትዮጵያም በአፍሪካ ያለውን ሰፊ ገበያ ለመጠቀም ዝግጅቷን አጠናቃለች ብለዋል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ጸጋ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ ንግድ ፖሊሲ ማዕከል አስተባባሪ ፕሮፌሰር መላኩ ደስታ በበኩላቸው፣ኢትዮጵያ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነቱን መተግበሯ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ የአፍሪካ አገራት ወደ አገራቸው በሚያስገቧቸው ምርቶች ላይ የሚጣለውን ቀረጥና ሌሎች ከቀረጥ ውጭ ያሉ ተግዳሮቶችን በሂደት በመቀነስ የአፍሪካ የእርስ በርስ የንግድ ትስስር ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026