አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2017(ኢዜአ)፦የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ኢንተርፕራይዞች ከሀገር ባለፈ በዓለም ደረጃም የተሻለ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
ርዕሰ-መስተዳድሩ በብዝሃ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ኢንተርፕራይዞች የተሻለ እድገት እያስመዘገቡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ የተካሔደ ሲሆን በተለያዩ የዕድገት ተኮር ዘርፎች ውጤታማ ለሆኑ ኢንተርፕራይዞችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር በወቅቱ እንደተናገሩት ኢንተርፕራይዞች በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በመታገዝ የውስጥ ፀጋዎችን ተጠቅመው ተኪ ምርቶችን በማምረት ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ የክልሉ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ኢንተርፕራይዞች ከሀገር ባለፈ በዓለም ደረጃ በኢኮኖሚ የበለጸጉ እንዲሆኑ ምቹ ምህዳር እየፈጠረ መሆኑንም አንስተዋል።
ልፋትን ወደ ውጤት ፣ፀጋን ወደ ሀብት በመቀየር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ኢንተርፕራይዞቹ ጠንክረው ሊሠሩ እንደሚገባ ጠቅሰው ፤ ለዚህም አመራሮች፣ ቤተሰብ ፣የፋይናንስና የትምህርት ተቋማት መደገፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክልሉ በርካታ ኢንተርፕራይዞች በሌማት ትሩፋትና በሌሎች መስኮች ተኪና ወጪ ምርቶችን በማምረት ዕድገትን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
መንግስት ለኢንተርፕራይዞች ለውጥ ብድር ፣የመስሪያና መሸጫ ስፍራዎችን በማመቻቸት እንዲሁም ክህሎት መር ስልጠና በመስጠት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
ከክልሉ ኢንተርፕራይዞች መካከል ከጌዴኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ወረዳ የ"ዘፍጥረት" ቡና ችግኝ ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ታሪኩ ሎሌ በሰጠው አስተያየት፤ ተደራጅተው የቡና ችግኝ በማፍላት ለአርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በመሸጥ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ገልጿል።
መንግስት ባመቻቸላቸው 50 ሺህ ብር ብድር በመታገዝ በሁለት ዓመታት ውስጥ ካፒታላቸውን አምስት ሚሊዮን ብር ማድረስ እንደቻሉ አስረድቷል።
በመድረኩ በተለያዩ የዕድገት ተኮር ዘርፎች ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን፤ ምርቶቻቸውን የሚያሳይ የፎቶ አውደ-ርዕይ ቀርቦ ተጎብኝቷል።
ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክ ላይ የክልልና የዞን አመራር አካላት ፣በክልሉ ግንባር ቀደም የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና የፋይናንስ ተቋማት ተሳተፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025