አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ)፦የሃላላ ኬላ ሎጅ ተደብቆ የነበረውን የቀደምት አባቶች ታሪክ በመግለጥ ለአካባቢው ማህበረሰብ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ፍሰት ከፍተኛ አቅም መፍጠሩን የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ገለጹ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በገበታ ለሀገር የኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሃላላ ኬላ ሎጅ በሚያዚያ 2015 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ይታወሳል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ግልገል ጊቤ-3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ተንተርሶ የተገነባው የሃላላ ኬላ ሎጅም በቱሪስት መዳረሻነት የሚያገለግል ድንቅ የመስህብ ስፍራ ሆኗል።
የሃላላ ኬላ ሎጅ ወደ ስፍራው ለሚያቀኑ ቱሪስቶች ታሪክ፣ተፈጥሮና ዘመናዊ የግንባታ ጥበብ ተሰናስለው ውብ ገጽታን በፈጠሩበት አስደናቂ የዓለም አቀፍ የመዳረሻ የተሻለ ጊዜ የሚያሳልፉበትን ዕድል ተፈጥሯል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ÷ ሃላላ ኬላ ቀደምት አባቶች ከ300 ዓመታት በፊት 1 ሺህ 225 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ባለ ሰባት ረድፍ ያለው የድንጋይ ግንብ የገነቡበት ታሪካዊ ስፍራ ነው ብለዋል።
በዚህ መነሻነትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የቀደምት አባቶችን የታሪክ አሻራ በሚገባው ልክ ማስታወስ የሚስያችል የሃላላ ኬላ ሎጅ ኢኮ-ቱሪዝም እንዲገነባ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የሃላላ ኬላ ሎጅ የዳውሮን ህዝብ ታሪክና ልማት በማስተዋወቅ በሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።
የለውጡ መንግስት ለአካባቢ ማህበረሰብ የፈጠረው የልማት ዕድልም የቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እየተፈጠረ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የሃላላ ኬላ ሎጅ የግልገል ጊቤ-3 የኤልክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ተንተርሶ መገንባቱም ወጣቶች በጀልባ መዝናኛና ሌሎች የስራ ዕድል መስኮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የሃላላ ኬላ ሎጅ ኢኮ-ቱሪዝም መገንባቱም የዳውሮን ህዝብ ባህላዊ የአመጋገብና የአኗኗር ሥርዓት በማስተዋወቅ በገጽታ ግንባታ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የሎጁ መገንባት ተደብቆ የቆየውን የቀደምት አባቶች የታሪክ አሻራ በመግለጥ በቱሪስት ፍሰት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል።
የዳውሮ ዞን ከሃላላ ኬላ ኢኮ ቱሪዝም በተጨማሪ በዳውሮና ኮንታ ዞኖች መካከል የሚገኘው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ ለቱሪዝም ልማት አቅም የሚሆኑ ጸጋዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
በዚህም በዳውሮ ዞን መዋዕለነዋያቸውን ፈሰስ የማድረግ ፍላጎት ያላቸው አልሚ ባለሃብቶች በግብርና፣በሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት የሚችሉበት ሰፊ ዕድል መኖሩን መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025