አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2017(ኢዜአ)፦አሜሪካ የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋን በአፍሪካ እንድታስፋፋ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና(ዶ/ር) ጠየቁ ።
የአፍሪካና የአሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ በአንጎላ ርዕሰ መዲና ሉዋንዳ እየተካሔደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ካላት ከፍተኛ የካፒታል አቅም አኳያ በአፍሪካ የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋን እንድታሰፋና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ የትብብር አድማስ እንድታጠናክር ጠይቀዋል።
የትኛውም ብልህ ባለሃብት አሁን ኢንቨስትመንትን ሲያስብ አፍሪካን ማሰብ አለበት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም አፍሪካ ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ስለሆነች መሆኗን አሃዛዊ መረጃ ጠቅሰው አስረድተዋል።
ዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገራት መካከል ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአፍሪካ አገራት መኖራቸውን አንስተዋል።
ሰፊ ያልታረሰ መሬት እና የሃይል ሽግግር እውን ማድረግ የሚያስችሉ ማዕድናት መኖራቸው አህጉሪቱን ተፈላጊ ያደርጋታል ብለዋል።
በመድረኩ እኔን ሳይሆን መረጃውን እመኑ በማለት የሞገቱት የባንኩ ፕሬዝዳንት አሁን ላይ የመንግሥታቱን መረጃ በመጥቀስ አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ከ15 በመቶ እስከ 20 በመቶ የወጪ ተመላሽ ትርፍ የሚያስገኝ መሆኑን አስረድተዋል።
በጉባኤው ላይም ፕሬዝዳንቱ በአፍሪካ በኢኮኖሚ መስክ ላበረከቱት የአመራርነት ሚና እውቅና ተሰጧቸዋል።
እውቅናው የባንኩ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና(ዶ/ር) ላለፉት 10 ዓመታት የመሩት አህጉራዊ የፖሊሲ ባንክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻልና የአህጉሪቷ ልማት እንዲፋጠን ያበረከቱትን የአመራርነት ሚና ከግምት ያስገባ መሆኑም ተጠቅሷል።
በጉባኤው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ሚኒስትሮች፣ የመንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣የሁለቱም ወገን የቢዝነስ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025