የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ተሞክሮዎችን የማስፋት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 25, 2025

IDOPRESS

ዱራሜ ፡ ሰኔ 17/2017(ኢዜአ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርናውን በማዘመን ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን የማስፋትና አጠናክሮ የማስቀጠል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለፀ፡፡

"የግብርና ሴክተር ምሰሶዎችን በማሳካት የበለፀገ ቤተሰብ ለማየት እተጋለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በግብርና ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ዙሪያ ለግብርና ልማት ሰራተኞች የተዘጋጀ ስልጠና በዱራሜ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂን በማሸጋገር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡

የግብርና ሴክተሩን በመደገፍ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ እየተከናወነ ባለው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግብርናን በማዘመን ከድህነት ለመውጣት እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አመልክተዋል።

ውጤቶቹን የማስፋትና አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ረገድ የግብርና ባለሙያው ሀላፊነቱን የበለጠ መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡


ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተጀመረው ጥረት በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል።

በሀገራዊና በክልላዊ ኢንሼቲቮች ከዚህ ቀደም በክልሉ ያልተለመዱ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በስፋት ማምረት መቻሉን ጠቅሰዋል ።

በዚህም ቴክኖሎጂን በማሸጋገር የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉንም አመልክተዋል።

የግብርና ባለሙያው በዘርፉ እየተመዘገበ ለሚገኘው ስኬት ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኑን ጠቁመው ጥረቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል ።

የከምባታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሄራሞ በበኩላቸው በዞኑ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተደረገ ባለው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የኩታ ገጠም እርሻን የማስፋትና በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ዝርያን የማሻሻል ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡

የምርት ወቅቶችን በአግባቡ ከመጠቀም በተጨማሪ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም የዝናብ ወቅትን ከመጠበቅ የተላቀቀ አርሶ አደር ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በግብርና ትራንስፎርሜሽን የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለማሳካት ያሉ እድሎችን መጠቀምና ተግዳሮቶችን በመፍታት የላቀ እመርታ ማስመዝገብ መሆኑ ተጠቅሷል።

በስልጠናው 1ሺህ 500 የግብርና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን በክልሉ በሶስት ክላስተሮች ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የግብርና ባለሙያዎች ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ ተመላክቷል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025