ገንዳ ውሀ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን የግብርና ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ለዘመናዊ አስተራረስና ግብዓት አቅርቦት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ ጌትነት ካሳሁን፤ ዞኑ ገበያ ተኮር ምርቶችን በስፋት ማምረት የሚያስችል የእርሻ መሬት መገኛ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በ2017/2018 የምርት ዘመን 530ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በዘመናዊ መንገድ አርሶ አደሩንና ባለሃብቱን በማሳተፍ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
የሚመረተውም አኩሪ አተር፣ ሰሊጥ፣ ማሽላ፣ ጥጥ፣ ማሾ፣ ሱፍና ሌሎች ገበያ ተኮር ሰብሎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የግብርናውን ምርታማነት ይበልጥ ለማሳደግ ከ530 በላይ ትራክተሮችና በቂ ግብዓት መቅረቡን አመልክተው፤ ከዚህም 12 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመዋል።
በዘር ከሚሸፈነው ውሰጥ 434ሺህ ሄክታሩ በአርሶ አደሮች፤ ቀሪው በባለሃብቶች መሆኑን ተናግረዋል።
ከመተማ ወረዳ አርሶ አደር ዮሐንስ ስዩም በሰጡት አስተያየት፤ በዚህ የምርት ዘመን 10 ሄክታር መሬታቸውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ማዳበሪያን በመጠቀም በዘር የመሸፈን ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሽላና ጤፍ የሚያለሟቸው የሰብል ዓይነቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ ቃሲም አህመድ በበኩላቸው፤ 50 ሄክታር መሬታቸውን እስከ ሀምሌ አጋማሽ ድረስ በሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ጥጥና ማሽላ ለማልማት ከወዲሁ ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በዞኑ ባለፈው የምርት ዘመን 521ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ታርሶ ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025