የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በዞኑ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው

Jun 27, 2025

IDOPRESS

መቱ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ) በኢሉባቦር ዞን የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ።

በዞኑ በግንባታ ላይ የነበሩና ግንባታቸው የተጠናቀቁ 656 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በሁለት ምዕራፎች ለአገልግሎት ክፍት የማድረግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።


በመርሐ ግብሩም በ314 ሚሊዮን ብር የተገነባው የኢሉባቦር ዞን ገንዘብ ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ በመቱ ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በፕሮጀክቶቹ ማስመረቂያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻፊ ሁሴን እንዳሉት ፕሮጀክቶቹ የማህበረሰቡን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ እንዲሆኑ በትኩረት የተከናወኑ ናቸው ብለዋል።


በዞኑ በዓመቱ በግንባታ ላይ ከነበሩ 656 የተለያዩ ፕሮጀክቶች መካከል ግማሽ ያህሉ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉ የገለፁት ደግሞ የኢሉባቦር ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ ናቸው።

በዞኑ በአጠቃላይ በመንግስት በጀት፣ በሕብረተሰብ ተሳትፎ፣ በፕሮግራሞችና በአገልግሎት መርሐ ግብሮች በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በክረምቱ ወቅት ተመርቀው ለአገልግሎት የሚበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ ለብዙዎች የስራ ዕድሎች የተፈጠሩበት መሆኑን ጠቁመው፤ የሕብረተሰቡን ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል።


በ314 ሚሊዮን ብር የተገነባው የኢሉባቦር ዞን ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ሕንጻ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የተመቸ መሆኑንም አመልክተዋል።

የመቱ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገረመው ብርሃኑ በበኩላቸው በመቱ ወረዳ በክረምቱ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነቡ የገበያ ማዕከልና ሌሎች የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል።

አቶ ገረሙ በዛብህ በወረዳው የቡሩሳ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሲሆኑ በቡሩሳ ቀበሌ የተገነባው የገበያ ማዕከል ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለአርሶ አደሮች ተጠቃሚነት መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው ብለዋል።


ባለፉት ጊዜያት አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ የሚያቀርብበት ምቹ ሁኔታ እንዳልነበረውና ተጠቃሚነቱም በዚያው ልክ ውስን እንደነበርም አክለው ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ ከዚህ ቀደም የሚያመርተውን ምርት በቀጥታ ለተጠቃሚዎች እንዲሁም ለነጋዴው ለማቅረብ የሚችልበት አጋጣሚ ባለመኖሩ በሕገ ወጥ ደላሎች ሲበዘበዝ እንደነበር ያነሱት ደግሞ የዞኑ ነዋሪ አቶ ካሚል ሺፋ ናቸው።


የገበያ ማዕከሉ ለአርሶ አደሮች ብቻ ሳይሆን ለነጋዴዎችም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025