የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፍ ቀጣናዊ ትስስርን እና የጋራ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠች ነው

Jun 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ ) ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፍ ቀጣናዊ ትስስርን እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራትን አጠናክራ መቀጠሏን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፥ የክህሎት ልማት ዲፕሎማሲ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ባለፉት ዓመታት በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ነጻ የትምህርት እድሎች ለደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ሌሎችም የጎረቤት ሀገራት ዜጎች እየሰጠን ነው ብለዋል፡፡


ነጻ የትምህርት እድሎች የክህሎት ሰልጣኞቹ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያን ባህልና ገጽታ በማስተዋወቅ አምባሳደር እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የሆነ የስልጠና ማዕቀፍ በማዘጋጀት የእርስ በእርስ የክህሎት ልማት የስልጠና ዕድሎች እየተፈጠሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል በክህሎት ዘርፍ የልምድ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ልምድ መውሰዳቸውን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡


ባለፉት ዓመታት በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር ከማገዛቸው ባለፈ በዲፕሎማሲው ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ነው የጠቀሱት።

በኢትዮጵያ ቅድሚያ ለጎረቤት ሀገራት በሚለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ በክህሎት ዘርፍ የሚኖረውን ቀጠናዊ ትስስር ለማስፋት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት አምስት ዓመታት በየዓመቱ 250 ለሚደርሱ የጎረቤት ሀገራት ዜጎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የትምህርት ዕድል መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡


ተመርቀው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ተማሪዎች በሀገራቸው አሰልጣኞች፣ ዲኖች እንዲሁም የተለያዩ የስልጠና ተቋማት አመራሮችና ፖሊሲ አውጪዎች ሆነው በመስራት ላይ እንደሚገኙም አንስተዋል።

ከደቡብ ሱዳን የመጣው ተማሪ ጋሪማ ቤልቸር በኢንስቲትዩቱ እውቀትና ክህሎት ከማግኘት በተጨማሪ በትምህርቱ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገለት እንደሚገኝ ተናግሯል።


በትምህርት ቆይታውም በርካታ ኢትዮጵያውያን ጓደኞች ማፍራቱንና እንደ ሁለተኛ ቤቱ እንደሚሰማው ገልጿል።

ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን መልካምነትና እንግዳ ተቀባይነት እንደሚመሰክር አረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025