
ሀዋሳ ፤ሰኔ 21/2017 (ኢዜአ) ፡-የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፈላጊ ደንበኞች በፍጥነት ምላሽ የሚያገኙበት አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሲዳማ ሪጅን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ አገልግሎት የሲዳማ ሪጅን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኘት የሚጠይቁ አዲስ ደንበኞችን በ24 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል “ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን” የተሰኘ አሰራር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
በአገልግሎቱ ሁሉንም ሂደት ጨርሰው ለሚመጡ ደንበኞች በአንድ ቀን ቆጣሪ በማስገባት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ፈጣንና ቀልጣፋ አሰራር ተግባራዊ እያደረገ ነው።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የሲዳማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ፤ አገልግሎቱ የአዲስ ደንበኞችን ጥያቄ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት ባለፉት 11 ወራት ብቻ 11 ሺህ 23 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሲዳማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞች ተሳትፎና ቁልፍ ደንበኞች ኃላፊ ትዝታ አስናቀ፤ በዘመቻ እየተከናወነ ባለው አሰራር በርካቶች ተጠቃሚ ስለመሆናቸው አንስተዋል።
በተቋሙ ስታንዳርድ መሠረት አንድ ደንበኛ በ10 ቀናት ውስጥ ለጠየቀው አገልግሎት ምላሽ በመስጠት ላይ እንገኛለን ያሉት ኃላፊዋ ስኬታማ ስራ መሆኑንም ተናግረዋል።
አገልግሎቱን ካገኙ ደንበኞች መካከል የሀዋሳ ከተማ ነዋሪው አቶ ዜና ደመቀ፤ አሰራሩ እንግልት የሌለውና ሁላችንንም ያስደሰተ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት ለጥያቄው ምላሽ ለማግኘት የተለያዩ ምክንያቶች እንደነበሩ አንስተው አሁን ላይ ችግሩ ተፈትቶ የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

የብረታ ብረት ባለሙያ የሆነው ወጣት አሸናፊ ተስፋዬ፤ ለጠየቀው አገልግሎት በአንድ ቀን ቆጣሪ አግኝቶ የኃይል ተጠቃሚ በመሆኑ እየሰራ ባለው የብረታ-ብረት ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግሯል።
አገልግሎቱ ባለፉት 11 ወራት የሥነ-ምግባር ጥሰት ታይቶባቸዋል ባላቸው 48 ባለሙያዎቹ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱም ታውቋል።
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026