አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በክረምት ወራት በዘር ከተሸፈነው 135ሺህ ሄክታር መሬት 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ አስተዳዳሪ አብዱልሰላም ዋሪዮ ገለጹ።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በቦረና ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም በቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በክላስተር የለማ ስንዴን ጎብኝተዋል።
የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሰላም ዋሪዮ ለከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ ባደረጉት ገለጻ፤ በዞኑ ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ የክረምት ወራት የግብርና ልማት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም 135 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የዘር ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸው ከዚህ ውስጥም ከ56 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በክላስተር እየለማ መሆኑንና 5ሺህ ሄክታር በስንዴ ምርት መሸፈኑን ጠቁመዋል።
ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ጤፍ፣ ማሾ እና ሌሎች ሰብሎችን ማልማት መቻሉን በመግለፅ፥ ከዚህም 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የቦረና ዞን አሁን ላይ በተሻለ ምርታማነት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ የአርብቶ አደሩ የስራ ባህል እየተቀየረ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርታማነት እንዲያድግም መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በልማት ጉብኝቱ ከፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ከፍያለው ተፈራ እና ሌሎች የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025